ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ መከላከያ ወታደሮች የሳተላይት ንብረቴን ወደመብኝ አለ

0
95

የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችው በመቐለ ከተማ የሚገኘው መስሪያ ቤቱ በኢትዮጵያ መከላከያ ወታደሮች ንብረቴን ወድሞብኛል አለ፡፡

ዩኒሴፍ የኢትዮጵያ መከላከያ ወታደሮች የግብረሰናይ ድርጅቶች ቢሮ በኃይል ተገብቶ የሳተላይት ቁሳቁሶችን ማውደም የሚወገዝ ድረጊት ነው አለ፡፡

የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ሄነሪታ ሆልስማንፎር በድርጅቱ ማህበራዊ ድረገጽ ባወጡት መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ወታደሮች የዩኒሴፍ የስራ ቁሳቁሶችን  ማዉደማቸዉ የአዉሮፓ ህብረት መብት የሚጋፋ ነዉ ብለዋል፡፡ እንዲሁም ተግባሩ የአለምአቀፍ ሰብአዊ መብት ህግን የሚጣረስ መሆኑና ተግባሩ ኮኑኖታል፡፡

የዩኒሴፍ ዋነኛ አላማ በትግራይ የሚገኙ ጠኔ የተጋረጠባቸዉ ከ140 ሺህ በላይ ህጻናትን ማገዝ ነዉ፡፡ በየትኛዉም መስፈርት ድርጅታችን የጥቃት ኢላማ መሆን አልነበረበትም ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል ሲሳተፉ የነበሩት ሁሉንም ሀይሎች በህግ እንዲገዙ አነጋግሪያለሁ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ሰብአዊነት ላይ የሚሰሩ ኤጀንሲዎች የመጠበቅ ሀላፊነት እንዳላቸዉ አሳዉቀናቸዋል ብለዋል፡፡ 

በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑት ኃይሎች ሰብአዊ መብት ላይ የሚሰሩ ኤጀንሲዎችን መውረስ፤ ጣልቃ መግባትና ስራቸውን ማስተጓጎል የለባቸውም ያሉት ሄነሪታ የሰብአዊ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን ጭምር ተደራሽ እንዲሆን መፍቀድ አለባቸው ብለዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 22/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ