የትግራይ ክልል መዲና መቐለ በህወሓት ቁጥጥር ስር መሆንዋ ተሰማ

0
20

ለበርካታ የሰብዓዊ ጉዳት መንሰኤ መሆኑ የሚነገረለት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት)ና የፌዴራል መንግስት ጦርነት ላለፉት ስምንት ወራት መካሄዱ ይታወቃል፡፡

የትግራይ ህዝብ በሁለቱ ኃይሎች የነበረ የከረረ ጦርነት ለብዙ ችግርና እንግልት ተዳርገዋል በሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለዋል፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሙተዋል እንዲሁም ጸታዊ ጥቃት ደርሶባቸውዋል፡፡

በሁለቱ ኃይሎች በኩል የነበረው ውግያ ተከትሎ ህውሓት በትላንትናው ዕለት ሰኔ 21 2013 ዓ.ም መቐለ መቆጣጠሩ የህውሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡

በፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል ሲደረግ የቆየው ጦርነት አሁን የፌዴራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ወስኛለሁ ሲል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ኃይሎች ከከተማዋ መውጣት መጀመራቸውን ተከትሎ በህወሓት አመራሮች ዘንድ “የትግራይ ኃይል” ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ መቐለ ከተማ እየገቡ መሆኑን የዶቼ ቬሌና የሮይተርስ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈ ቤት ከክልሉ ግዜያዊ መስተዳድር ለፌዴራል መንግስቱ የቀረበው የተናጠል የተኩስ አቁም ተቀባይነት አግኝቷል ሲል ትናንት ማምሻውን ገልጿል።

በመቀለ ከተማ ጎዳኖዎች ላይ ዳግም እንደታዩ የተነገራለቸው የትግራይ ሀይሎች ከተማዋ ዳግም በእጃቸው መግባትዋን ለአለም አቀፍ ሚዲያዎች ማሳወቅ ጀምረዋል።

በቅርቡ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብር የተፈረጀው የህውሃት ቃል አቀባይ የሆኑት ጌታቸው ረዳ “የትግራይ ዋና ከተማ ፣ መቀለ በእኛ ቁጥጥር ስር ነች” ሲሉ ለሮይተርስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

“ ሁሉም ጠላቶቻችን ትግራይን ለቀው እስኪወጡ እንዋጋለን “ ስትል ሌላኛዋ የቡድኑ ቃለ አቀባይ ሊያ ካሳ በሚዲያ በተሰራጨው የድምፅ ቅጂ ተሰምተዋል።

መንግስት በበኩሉ አርሶ አደሩ የክረምት ስራውን በሰላም እንዲሰራ የእርሻ ጊዜ እስኪጠናንቀቅ ድረስ የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት አውጃለሁ ብሏል።

በክልል የሚወሰኑ ቀጣይ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መንግስት የሰጠው ግልፅ ማብራሪያ የለም።

መቀለ በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር በቁጥጥር ስር መሆን አለመሆኗን በተመለከተም የኢትዮጵያ መንግሥት የሰጠው አስተያየት የለም።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 22/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ