በትግራይ በሰብአዊ ሰራተኞች ግድያ አጅጉን አዝኛለሁ – ሚሼል ባኬት

0
75

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል  ባኬት “በትግራይ  በሰብአዊ ሰራተኞች ግድያ  አጅጉን አዝኛለው  ገዳዮቹ በህግ ሊጠየቁ ይገባል “ብለዋል

“ሰሞኑ በትግራይ  ውስጥ በሶስት  የድንበር   የለሽ ግብረሰናይ ሠራተኞች ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ አዝኛለሁ”። የሰብአዊ እና የሰብአዊ መብት ሰራተኞች ሲቪሎች ናቸው። እናም  በጭራሽ  የግድያ ዒላማ ሊሆኑ አይገባም ብለዋል፡፡

 “እነዚህ አስደንጋጭ ግድያዎች የሰማነው በትግራይ ውስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች ዘገባዎች እየደረሱን ባለ ወቅት ነው ” ብለዋል ባለስልጧኗ።

 በሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ በተገደሉ ባልደረቦቻችን እና ስለተፈፀሙ  ሰብአዊ መብት ጥሰቶች  ሁሉ ወቅታዊ ፣ ግልፅ ፣ ጥልቅ ምርመራ ሊኖር ይገባል ፣ ወንጀለኞችም በህግ መጠየቅ አለባቸው ፡፡” በማለት ዛሬ  መግለጫ ሰጥተዋል።

ባለፈዉ ሳምንት በትግራይ ሦስት የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ሠራተኞች መገደላቸዉን ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ድረገጹ ላይ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው ዓብይ ዓዲ ተብሎ በሚጠራ “ህወሓት በሚንቀሳቀስበት አካባቢ” ነዉ ማለቱ ይታወሳል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዓብይ ዓዲ አካባቢ ህወሓት እንደሚንቀሳቀስ በመግለፅ  ሰራዊቱ ፥ “የበለጠ በራሳችን መንገድ የሚረጋገጥ ቢሆንም ፥ የህወሓት ታጣቂዎች ሰራተኞቹን ከመኪና አስወርደው እንደገደሏቸው ቅድመ መረጃ ደርሶናል” የሚል ማብራርያ እንደሰጠ ይታወቃል።

በፌዴራል መንግስት መንግስት ከሁለት ወር በፊት ሽብርተኛ በተባለው ህወሓት ስም ዛሬ ባወጣው መግለጫ የድንበር የለሽ ሀኪሞች ቡድን አባላትን ጨምሮ ንፁሃን ዜጎች የተገደሉት በኢትዮጵያ መካለከያ ሰራዊት ፤በኤርትራ ጦርና በአማራ ሚሊሻ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ወር መጀመሪያ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ሰራተኞች የትግራይ ሀይልን እየደገፉ ነዉ ማለቱ በማስታወስ ሰኔ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በቶጎጋ ላይ የደረሰዉን የአየር ጥቃት የዚህ ማሳያ ነዉ ብልዋል ድርጅቱ፡፡ የቶጓጎጋውን ጥቃት መከላከያ ሰራዊት በንፁሃን ላይ የተፈፀመ ሳይሆን በሞግበይ የሚመሩ አማፂያን ላይ የሰኔ 15 የሰማዕታት ቀንን ለማክበር በወጡበት የፈፀምሁት ነው ማለቱ አይዘነጋም።

በህወሓት ስም የወጣው መግለጫ ግን በተጨማሪም በመጋቢት ወር ላይ በጉዞ ላይ የነበሩትን በድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ሰራተኞች ፊት የተገደሉት ንጽኋን ዜጎች እንደ ማሳያ አስቀምጥዋል፡፡

 ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራም ጥሪ አቅርብዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 21/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ