ጆርድ ፍሎይድን የገደለው ፖሊስ የ22 ዓመት ከ6 ወር እስር ተፈረደበት

0
61

ባለፈው ዓመት ግንቦት ሚኒሶታ ውስጥ አፍሪካ አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው አሜሪካዊው ነጭ የቀድሞ የፖሊስ መኮንን 22 ዓመት ከስድስት ወር እስር ተፈረደበት።

የዴሪክ ቻውቪን ቅጣት “የተጣለበትን እምነት እና ኃላፊነት በማጉደል እንዲሁም በታየው ልዩ ጭካኔ” ላይ የተመሠረተ መሆኑን ዳኛው ተናግረዋል።

የ48 ዓመቱ ጆርጅ ፍሎይድ ህይወት ያለፈው ቻውቪን አንገቱ ላይ ለዘጠኝ ደቂቃዎች የህል ተንበርክኮ ተንፋሽ አሳጥቶት ከቆየ በኋላ ነበር።

ግድያው ዘረኝነትን እና የፖሊስ ጭካኔን ሚቃወሙ ዓለም አቀፍ ተቃውሞዎችን አስከትሏል።

የ45 ዓመቱ ቻውቪን ባለፈው ወር በሁለተኛ ደረጃ ግድያ እና በሌሎች ጥፋቶች ተከሶ ነበር። በችሎቱ ወቅት ግድያውን “በቅን ልቦና የተሠራ ስህተት” ሲሉ ጠበቃው ገልጸው ነበር።

በተጨማሪም ቻውቪን እንደ አጥቂ ወንጀለኛ እንዲመዘገብ እና በቀሪ ዕድሜው የጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳይሆን ታግዷል።

ከእሱ በተጨማሪ ሌሎች ሦስት የቀድሞ መኮንኖች የጆርጅ ፍሎይድን መብቶች በመጣስ በተናጠል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የፍሎይድ ቤተሰቦች እና ደጋፊዎቻቸው ውሳኔውን በደስታ ተቀብለዋል።

ጠበቃው ቤን ክሩም በትዊተር ገጻቸው “ይህ ታሪካዊ ቅጣት ተጠያቂነትን በማስፈን የፍሎይድ ቤተሰቦችን እና አገራችንን ወደ ፈውስ አንድ እርምጃ እንዲጠጉ ያደርጋቸዋል” ብለዋል።

የፍሎይድ እህት ብሪጅት ፍሎይድ ውሳኔው “የፖሊስ ጭካኔዎች በመጨረሻም በደንብ እየታዩ መሆናቸውን ቢያሳይም ገና ብዙ የሚቀር መንገድ አለ” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፍርዱ “ተገቢ ይመስላል” ብለው ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 19 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ