ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙርያ የተፈጠረውን አለመግባባት በወታደራዊ መንገድ የመፍታት ፍላጎት የላትም – ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

0
208

የመከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ኢትዮጵያ በግድቡ ጉዳይ ከሱዳን እና ከግብፅ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት በወታደራዊ መንገድ የመፍታት ፍላጎት እንደሌላት ተናገሩ፡፡

ነገር ግን ግብጽና ሱዳን ከሰላማዊ ድርድር አልፎ ወታደራዊ አማራጭን የሚጠቀሚ ከሆነ ኢትዮጵያ ለዚህ ሁኔታ ዝግጁነት እንዳላት ተናግረዋል።

ሌ/ጄኔራል ባጫ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ያለውን አለመግባባት በወታደራዊ መንገድ ይፈታ እንደሆነ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ “ለአገሬ የውሃ ጉዳይ ለጦርነት መንስኤ ሊሆን አይገባም ፤ ስለሆነም መፍትሄው ወታደራዊ ሊሆን አይችልም ፣ ከሁሉ የተሻለው መፍትሔ በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚደረገው ውይይቱ ነው” ብለዋል።

 አክለውም ፥ የግብፅ ወገን ችግሩን በድርድር መፍታት አይፈልጉም ፤ ለውይይት ይመጣሉ ሁሉንም ሃሳብ ውድቅ ያደርጋሉ። በእኔ እይታ የተሻለው መፍትሄ ድርድር ነው፤ ችግሩን በወታደራዊ መንገድ መፍታት አይችሉም” ሲሉ ተናግረዋል።

ሌ/ጄኔራል ባጫ ይህን የተናግሩት በሩስያ ሞስኮ በ9ኛው የዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ በኃላ ከሩስያ አር ቲ ቴሌቫዥን ጋር ባደረጉት ቃለምምልልስ ነው፡፡

ሌ/ጄኔራል ባጫ ግብፆቹ ግድቡን ለማጥቃት አይሞክሩም፤ ነገር ግን ቢሞክሩት እንኳን ችግሩን ሊፈቱ ወይም ግድቡን ሊያጠፉት አይችሉም፤ ግድቡ በቦንብ እና በተዋጊ ፕሌኖች ሊወድም አይችልም የግድቡን ጥንካሬ እነሱም ያውቁታል” ብለዋል።

በተጨማሪ ሌ/ጄኔራል ባጫ “ችግሩን በውይይት እንፈታዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ዝግጅት ማድረጉን ይህ ደረጃ ሲያበቃም ሁሉም ነገር ጥሩ እንደሚሆን እንዲሁም ሁሉም አካል በግድቡ ግንባታ ላይ ሳይሆን በውሃ ክፍፍሉ ላይ በሚቀርቡት ሃሳቦች ላይ መወያየት ይመጣሉ ብለዋል።

ሌ/ጄኔራል ባጫ ኢትዮጵያ ለወታደራዊ መፍትሄ ዝግጁ ስለመሆና ለቀረበላቸው ጥያቄ ፥ “አዎ! እያንዳንዱ ሀገር ፥ ሀገሪን ለመከላከል ዝግጁ ነው እናም ሉኣላዊነታችንን ሊዳፈር የሚሞክር ጠላትን ሁሉ ለመመከት ዝግጁ ነን፤ ለመከላከል ዝግጁ ነን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሞስኮው የዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ በኩል የህዳሴው ግድብ ጉዳይ አለመነሳቱን ጠቁመዋል።

ነገር ግን ሌ/ጄነራሉ ፥ “ሩስያ በግድቡ ዙሪያ ያላትን ምልከታ እናውቃለን፤ ሁለቱም ወገኖች ችግሩ በወታደራዊ መንገድ ሳይሆን በንግግር እንዲፈቱት ትፈልጋለች፤ እኛም የሩስያን አቋም እናደንቃለን” ብለዋል።

በመጨረሻም ሌ/ጄነራል ባጫ፤ የኢትዮጵያ ልዑክ ከግብፅ ወገን ጋር በሞስኮ ምንም ዓይነት ስብሰባ አለመደረጉን ያረጋገጡ ሲሆን ነገር ግን ለውይይት ዝግጁ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ከአር ቲ ጋር ያደረጉት ቃለምምልልስ ከተሰራጨ በኃላ ግብፅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስተያየት ሰጥታለች። 

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሚ ሽኩሪ ግብፅ በግድቡ ዙርያ ያሉትን አለመግባባቶች በሰላማዊ ድርድር ለመፍታት ትሞክራለች ነገር ግን የውሃ ጥቅሟን የሚነካ ማንኛውም ኃይል ላይ አትታገስም ብለዋል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 19 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ