በቶጎጋ በንጽኋን ዜጎች ላይ የደረሰዉ የአየር ጥቃት የአለም የጤና ድርጅት አወገዘ

0
199

ሰኔ 15ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ዋና ከተማ የመቐለ ከተማ 25 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘዉ የቶጎጋ ገባያ ላይ የተፈጸመዉ የአየር ደብዳብ ከ33 አመታት በፊት በተመሳሳይ ቀን ሰኔ 15 ፤1980 ዓ.ም በሓዉዜን ከተማ የተደረገዉ ደብዳብ ጋር ብዝዎች ያመሳስሉታል፡፡

በቶጎጋ ለመገበያየት በወጣዉ ህዝብ ላይ የደረሰዉ የአየር ጥቃት ብዝዎችን ገድልዋል በመቶዎች የሚቆጠሩት ንጽኋን ዜጎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሷል፡፡

ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የጤና ባለሞያዎችና አምቡላንሶች ወደ አካባቢዉ እንዳይሄዱ መከልከላቸው በቦታው ለመሄድ ተልኮ የተከለከሉ የጤና ባለሞያዎች መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

የአለም የጤና ድርጅት በቶጎጋ በንጽኋን ዜጎች ላይ የደረሰዉን ጥቃት አዉግዝዋል፡፡

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም በወቅታዊ የኮቪድ-19 የአለም ሁኔታና የክትባት ስርጭት በሚመለከት ለጋዜጠኞት በሰጡት መግለጫ የቶጎጋ ጥቃትን አንስተዋል፡፡

“በትግራይ ክልል የመቐለ ከተማ ዉጪ በሚገኘዉ ገበያ በደረሰዉ ጥቃት ንፅኋን ዜጎች ላይ ጉዳት አድርሷል፤ አምቡላንሶች ከአንድ ቀን በላይ ወደ ቦታዉ ሄደዉ የህክምና እርዳታ እንዳይሰጡ ተከልክለዋል” ብለዋል ዶ/ር ቴድስ አድሓኖም፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ለሆስፒታሎች የህይወት አድንና ለቀዶ ጥገና የሚዉሉ የህክምና ቁሳቁሶች እርዳታ እንደሚያረግ ተናግረዋል፡፡

በየትኛዉ ቦታ በንጽኋን ዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ያወገዙት ዋና ዳይሬክተሩ ከዛም አልፎ አፋጣኝ የህክምና እርዳታ እንዳያገኙ መከልከል ተቀባይነት የሌለዉ ተግባር ነዉ ፤ ምክንያቱም የብዝዎች ህይወት እንድናጣ ያደርገናል ብለዋል፡፡

የአለም ተቋማት እንዲህ ቢሉም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ጥቃቱ በሚመለከት በሰጡት መግለጫ ሰኔ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. “የሰማዕታትን ቀን እናከብራለን ብሎ የተሰበሰበ” እና “ጄኔራል ምግበ የሚባል እመራዋለሁ የሚል ጦር” ላይ በጦር አውሮፕላን ላይ ነዉ ድብደባ የፈጸምነዉ ማለታቸዉ ሚዘነጋ ጉዳይ አይደለም፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 19 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ