በትግራይ የቀጠለው ጦርነት አፋጣኝ ተግባራዊ እርምጃ የሚጠይቅ ነው – አንቶንዮ ብሊንከን

0
133

በትግራይ ክልል የቀጠለው ጦርነት እና ሰብዓዊ ቀውስ አፋጣኝ ተግባራዊ እርምጃ የሚጠይቅ ነው ሲሉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንከን በትላንትናው ዕለት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በፌደራል መንግስትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) መካከል በተቀሰቀሰ ጦርነት ስምንት ወራት አስቆጥረዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹኃን ዜጎች ሂወታቸው አጥተዋል እንዲሁም ብዝዎችም ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት በሺዎች ሚቆጠሩ ሴቶች የጾታዊ ጥቃት ፤አካላዊና ስነሉበናዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ አሁንም ቢሆን ጦርነቱ በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠሉ የአለማቀፍ ድርጅቶችና ሚድያዎች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት ፤የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ እንዲወጣ፣ የተፈፀሙ ከፍተኛ ወንጀሎች እንዲመረመሩና ለሰብዕዊ እርዳታ ያልተገደበ መንገድ እንዲከፈትም ጠይቋል።

በተጨማሪም ምኒስትሩ የሰኔ 14ቱ 6ኛ ሃገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በመግለጫቸው ላይ አካተዋል፡፡

የሰኔ 14ቱ ምርጫ ኢትዮጵያ ከፍተኛ አለመረጋጋት ውስጥ ባለችበት እና የምርጫው ሂደት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ነጻና ፍትሃዊ ባልሆነበት ሁኔታ ተካሄድዋል ብለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፣ ምርጫው ታዋቂ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ከምርጫው መገለላቸው፣ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች በታሰሩበት እና በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭት ባለበት ሁኔታ መካሄዱን ገልጿል።

የሃገሪቱን ሉዕላዊነት፣ አንድነትና ህገ- መንግስታዊ ስርዓት ለማስጠበቅ ሁሉን- አቀፍ ጥረት በማድረግ ብሄራዊ መግባባት ላይ መድረስ የግድ እንደሚልም ነው የጠቆመው።

በዚህ የድህረ ምርጫ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ መሪዎች ሁከትን እንዳይቀበሉ ሌሎችን ወደግጭት የሚያነሳሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡም ሚኒስትሩ አሳስቧል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 19 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ