በትግራይ ሦስት የኤም ኤስ ኤፍ ሠራተኞች መገደላቸው አስደንጋጭ ድርጊት ነው – አሜሪካ

0
69

በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ሦስት የበጎ አድራጎት ሰራተኞች ላይ ስለተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የአሜሪካ መንግስት በግድያው እንዳዘነ በዋጠው መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በሰብዓዊ ሠራተኞች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሁሉ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቆ ይህንንም ድርጊት መቆም እንዳለበት ባወጣው መግለጫ ገልጽዋል፡፡

በተጨማሪም መግለጫው ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ እና ወንጀለኞቹ ለፈጸሙት ግድያ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በመጨረሻ የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን ደህንነት የማረጋገጥ እና ሰብአዊ ዕርዳታ ነፃ እና ያልተገደበ ተደራሽነትን የማግኘት ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳልም ብሏል የአሜሪካ መንግስት፡፡

የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኞች ዜጎችን በነጻነት መርዳት እንዲችሉ ፣ ተጨማሪ ስቃይን ለመከላከል እና ረሃብን ጨምሮ ብዙ ተግዳሮቶችን መፍታት እንዲችሉ ጦርነቱ መቆም እንዳለበት የአሜሪካ መንግስት አሳስበዋል፡

በጥቃቱ የተገደሉት የህክምና እርዳታ ድርጅቱ ባልደረቦች በየካቲት ወር ላይ በድርጅቱ በረዳት አስተባባሪነት ሥራ የጀመረው የ31 ዓመቱ ዮሐንስ ሃለፎም፣ በግንቦት ወር ለግብረ ሰናይ ድርጅቱንመሥራት የጀመረው የ31 ዓመቱ ሹፌር ቴድሮስ ገብረ ማሪያም እና ለዓመታት የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪዋ የ34 ዓመቷ ስፔናዊት ማሪያ ኽርናንዴዝ ናቸው።

ጥቃቱ በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት  ጥቃቱ የተፈጸመው ዓብይ ዓዲ ተብሎ በሚጠራ “ህወሓት በሚንቀሳቀስበት አካባቢ” መሆኑንና በህውሓት አባላት መፈጸሙ አመልክቷል።

በሦስቱ የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ላይ ግድያውን ማን እንደፈጸመ አስካሁን ከገለልተኛ ወገን የተሰጠ ማረጋገጫ የለም።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 19 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ