ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትጵያውያንን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ዘመቻ ተጀመረ

0
56

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያንን በወደ ሀገር ቤት የመመለስ ዘመቻ በዛሬው እለት መጀመሩን በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

በህገ ወጥ መንገድ የሳዑዲ አረቢያን ድንበር ጥሰው የገቡ እንዲሁም የሳዑዲ የመኖርያና የሥራ ፈቃድ ህግጋትን ተላልፈው በመገኘታቸው ከአንድ አመት በላይ በእስር የቆዩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ይታወቃል።

በቅርቡ መንግስት እነዚህ እስረኞች በሙሉ ወደ አገር እንዲገቡ ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ ብዛት ያላቸው በረራዎች ከሳዑዲ ወገን ጋር በመነጋገር የሚመቻቹ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል።

ይህን ለማሳካት የሁለቱ አገራት መንግስታት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቋሞ ዜጎችን በስፋት ወደ አገር የመመለስ ሂደት ለማሳካት ከኢትዮጵያ ወገን ቀዳሚ ልዑክ ቡድን ተልኮ ከሳዑዲ አረቢያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ ዜጎችን የማስመለስ ስራ መመቻቸቱንም ገልጿል።

በዚሁ መሰረት ከሰኔ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በየቀኑ እስከ ስድስት በሚደርሱ የሳዑዲና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች በማቆያ ጣብያዎች የነበሩ ዜጎች የሚመለሱ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲም በተለያ ማእከላት ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮፕያውያንን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ስራ መጀመሩን አስታውቋል ሲል አል ዐይን ዘግቧል።

በዛሬው እለት ከ2 ሺህ በላይ ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ የተባለ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት 6 በረራዎች በማድርግ ዜጎች ለአሀራቸው እንዲበቁ ማድርግ መጀመሩን ኤምባሲው አስታውቋል።

በዚህ የማስመለስ ሥራ ቅድሚያ ወደ አገር እንዲገቡ የተደረጉት ሴቶች፣ ህጻናት እና ታማሚ ዜጎች መሆናቸውንም ነው የገለጸው።

መንግስት ከሳኡዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመሆን በተለያዩ ማቆያ ማእከላት ውስጥ የሚገኙ 40 ሺህ ኢትዮፕያውያንን በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ በተከታታይ ወደ አገር እንደሚመልስም ኤምባሲው አስታውቋል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 19 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ