የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የህወሓት ቡድን አባላት ህንጻዎች ላይ ዉሳኔ አስተላለፈ

0
22

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕወሃት ቡድን አባላት ሕንጻዎች በገለልተኛ አስተዳዳሪ ተይዘዉ እንዲተዳደሩ ወስኛለው አለ፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑት አቶ ዓምአንተ አግደዉን ጠቃሶ አቃቢ ህግ እንዳሳዋቀው ዉሳኔው የተሰጠዉ የሽብር ቡድኑ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የወንጀል ምርመራና የሀብት ጥናት እየተከናወነ መሆኑን መነሻ በማድረግ ነው ብሏል።

ቡድኑ ከሕንጻዎቹ የሚያገኘዉን ገቢ የሽብር ተግባሩን ፋይናንስ ለማድረግ እንዳያዉል ለመከላከል፣ በተጠረጠሩበት የሽብር እና ሌሎች ወንጀሎች በፍ/ቤት ጥፋተኛ ሆነዉ ከተገኙ ሀብታቸዉ የሚወረስ በመሆኑ ተጠብቆ እንዲቆይ፣ የሽብር ቡድኑ በመከላከያ የሰሜን ዕዝ ሀብት፤ በተለያዩ መሰረተ ልማቶችና ስቪል ተቋማት ላይ ላደረሰዉ ዉድመትና ጉዳት ለማካካሻነት የሚዉል በመሆኑ ነው ማለታቸው ተገልፅዋል።

እንዲሁም የተጠርጣሪዎችን ንብረት የያዙ አካላት የሚፈጽሙትን ምዝበራ ለመከላከል ሲባል በተጠረጠሩበትና በተከሰሱበት ወንጀል ፍ/ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ገለልተኛ አካል እንዲያስተዳድራቸዉ ዐቃቤ ሕግ ለፍ/ቤት አቤቱታ ማቅረቡን ተከትሎ ነዉ ሲል አሳውቋል፡፡

ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ሕግን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ ሕንጻዎችን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥር የሚገኘዉ ኮመርሽያል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እንዲያስተዳድር ዉሳኔ ምስጠቱን አሳውቋል ፡፡

በዚህ ዉሳኔ አስተዳዳሪ የተሾመላቸዉ የንግድና መኖሪያ ሕንጻዎች አጠቃላይ ብዛት ከ 30 በላይ ነው ያለ ሲሆን ከእነዚህ መካከል፡-

-በ ጄ/ል ፃድቃን ገ/ተንሳይ ስም አዲስ አበባ የሚገኙ 2 (ሁለት ህንጻዎች) ፣

-በ ጄ/ል አበበ ተክለሃይኖት ስም አዲስ አበባ የሚገኝ አንድ G+5 ሕንጻ (ወለላ ሕንጻ)፣

-በ ብ/ጄ ምግበ ሃያለ ስም አዲስ አበባ እና መቀሌ የሚገኙ 2 (ሁለት) ሕንጻዎች፣

-በ ብ/ጄ ታደሰ ወረደ ስም መቀሌ የሚገኙ 2 (ሁለት) ሕንጻዎች፣

-በ ብ/ጄ ተክላይ አሸብር ስም አዲስ አበባ የሚገኝ G+5 ሕንጻ (ብሌን ሕንጻ)

-በ ብ/ጄ ዮሀንስ ወ/ጅወርጊስ ስም መቀሌ የሚገኙ 3 (ሦስት) ሕንጻዎች፣

-በሜ/ጄ ሕንጻ ወ/ጊወርጊስ ስም መቀሌ የሚገኝ 1 (አንድ) ሕንጻ፣

-በሜ/ጄነራል ኢብራሂም አብዱል ጄሊል ስም መቀሌ የሚገኝ 1 (አንድ) ሕንጻ እና

-በሃይለ ተስፋኪሮስ ገ/ሕይወት ስም መቀሌ የሚገኙ 3 (ሦስት) የነዳጅ ማደያዎች ይገኙበታል ሲል ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል ፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 18 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ