የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ ሚደረገውን በረራ አቋረጠ

0
96

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ እንደገና ባገረሸው ውጊያ ምክንያት ወደ መቐለ የሚያደረገውን የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት አቋረጠ።

አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው ከማክሰኞ ሰኔ 15 ጠዋት ጀምሮ እንደሆነ የድርጅቱ እና የጉዞ ወኪል ሰራተኞች ተናግረዋል። 

በትላንትናው እና በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ፤ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በረራ የነበራቸው መንገደኞች ከጉዟቸው መስተጓጎላቸውን ተናግረዋል፡፡

ለተጓዦቹ በረራ መሰረዙ የሚነገራቸው አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ እንደሆነ በመቐለ አየር ማረፊያ የሚሰሩ አንድ ባለሙያ ገልጸዋል። “ጉዳዩ የደህንነት ጉዳይ ስለሆነ ለሰራተኞችም የሚነገረው በድንገት ነው ሲሉ እኚሁ ባለሙያ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ውጊያ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለአንድ ወር ከግማሽ አቋርጦት የነበረውን በረራ የጀመረው በታህሳስ ወር አጋማሽ ነበር።

አየር መነገዱ በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ወደ መቐለ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ በቀን እስከ አምስት ጊዜ በረራዎችን እንደሚያርግ ነው የተገለጸው።

የመጨረሻው በረራ የተደረገው 53 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ከመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ወደ አዲስ አበባ ማክሰኞ ከምሽቱ 12 ጉዞውን ባደረገው አውሮፕላን ነው።

ከዚያ በኋላ የነበሩት በረራዎች የተቋረጡት፤ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ አንድ የጦር አውሮፕላን ግጀት በተባለ አካባቢ በአየር ላይ ተመትቷል መባሉን ተከትሎ መሆኑን እኚሁ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ያብራራሉ ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር  ዘግቧል። 

አውሎ ሚድያ ሰኔ 18 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ