ኢትዮጵያን የሚታደግ መንግስት በሰራዊቱና በፕሬዚዳንቷ መመስረት አለበት – ኦነግ

0
148

ኦነግ የኢትዮጵያ  መከላከያ ሰራዊት እና የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሰላምን በማረጋገጥ ኢትዮጵያን የሚታደግ መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ፡፡

በቅርቡ የተካሄደው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ያልተሳተፈው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምርጫው ሂደትና ውጤት በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በዋናነት በመንግስት መዋቅሮች ምክንያት የሚነሱትን ዓላማዎች እና ግድፈቶች እያወቁ በምርጫው ላይ ጥቂት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል ነው ያለው ኦነግ በመግለጫው፡፡

ስለሆነም ይላል ፓርቲው እነዚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው በተመለከቱ ጉዳዮች እና በውጤቱ ላይ በልዩነቶች ላይ ማንኛውንም ሁከት ከማነሳሳት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል።

በእንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ላይ ማንኛውንም የሕዝብ አመፅ ማነሳሳት በፖለቲካዊም ሆነ በሞራል ተቀባይነት የለውም ያለው ኦነግ ይልቁንም ሕዝቦቻችንና ሀገሪቷ ለገጠማት ቀውሶች መፍትሄ የሚፈለግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል።

ስለሆነም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊያተኩሩባቸው ይገባል በማለት ስድሰት የውሳኔ ሃሳቦችን አስቀምጧል።

በባለድርሻ አካላት መካከል ውጤታማ ውይይት እንዲጀመር መንገዱን ለመክፈት እንደ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዲሪ) የመታደግ መንግሥት ጊዜያዊ አካል ለማቋቋም መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል ፓርቲው፡፡

ኦነግ የመፍትሔ ሃሳብ ነው ብሎ ያቀረበውን አንዱ  የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት እና የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሰላምን በማረጋገጥ የኢትዮጵያን የመታደግ መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላ አገሪቱ የሚካሄዱ ጦርነቶችንና ግጭቶችን በአስቸኳይ እንዲያቆምና የኤርትራ ወታደሮችና የደህንነት ሰራተኞቻቸው ከኢትዮጵያ በአፋጣኝ እንዲወጡ ነው ያለው ኦነግ ።

ለዚህም የኢትዮጵያ ህዝቦች እና ሁሉም የፖለቲካ አካላት ግዴታቸውንና ሃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን ነው ያለው ኦነግ።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ለፖለቲካዊ ውይይት መንገድ የሚከፍት የሽግግር ስርዓት ለመዘርጋት በሁሉም ባለድርሻ አካላት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል

ኦነግ የኦሮሚያ ክልል ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ከሁሉም ብሄሮች እና ብሄረሰቦች ጋር በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖርና ትርጉም ያለው የፖለቲካ ውይይት እውን ለማድረግ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 18 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ