በትግራይ የወደቀው የጦር አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ነው – ኮሎኔል ጌትነት

0
603

ባለፈው ሳምንት ረብዕ ዕለት ከመቐለ በስተ ደቡብ ምዕራብ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ዓዲ ዓቓላ በምትባል አከባቢ አንድ የጦር አውሮፕላን መውደቁ በማህበራዊ ድረገጽ ሲሰራጭ ቆይተዋል፡፡

የጦር አዉሮፒላኑ በትግራይ ክልል እየተዋጋ እንዳለ የሚታንበት ኃይል ተመታ እንደወደቀች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲሰራጭ ነበር፡፡

የጦር አውሮፕላንዋ በተመለከተ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በስአቱ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ 

የኢትዮጳያ መከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ የሆኑት ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የጦር አውሮፕላኑ ወደቀችበት ከተባለ ከቀናት በኋላ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በህውሓት ተዋጊዎች ቡድን ተመታ ሳይሆን በቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው የወደቀው ሲሉ ቃላቸውን  ሰጥተዋል፡፡

የህውሓት ተዋጊ ቡድኖች የጦር አውሮፕላኑ በቴክኒክ ችግር ሳይሆን ተመታ እንደወደቀ ገልጸዉ መሳሪያና የኤርትራ ሠራዊትን የደንብ ልብስ የለበሱ ወታደሮችን ጭምር ጭና ከባህርዳር ወደ መቐለ ስትጓዝ እንደነበር ነው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ  እንደተናገሩት ከሆነ አውሮፕላኑ የወደቀው ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል።

አማጺኑ እንዳሉት ሳይሆን “በሌሎችም አውሮፕላኖች ላይ እንደሚያጋጥመው ሁሉ አውሮፕላኑ በቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው የወደቀው” ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ጨምረውም ከወደቀው አውሮፕላን ጋር በተያያዘ የደረሰ ጉዳት ካለ በቅርቡ እንደሚገለጽ በመጥቀስ ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል ውስጥ የተጠናከረ ውጊያ መካሄዱ የተነገረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በገበያ ቦታ ላይ ጥቃት ፈጽሞ በርካታ ሠላማዊ ሰዎችን ገድሏል እንዲሁም አቁስሏል በሚል ተከሷል።

ነገር ግን ሠራዊቱ ጥቃቱም በገበያ ቦታ ላይ ሳይሆን ኢላማ ያደረኩት ህውሓት ተዋጊዎች  ላይ ነው በማለት ክሱን አስተባብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል ልዩ ቦታው ዓዲ ዓቓላ በተባለ ቦታው የወደቀ አውሮፕላን ሔርኩለስ ሲ-130 የተባለ የጦር አውሮፕላን እንደሆነ በተለያዩ በማህበራዊ ድረገጽ ትስስር ላይ የተሰራጩ ምስሎችና  ቪድዮች ያመላክታሉ፡፡

የህወሓት ኃይሎች ከመንግሥት ሠራዊት ጋር በሚያደርጉት ፀረ ማጥቃት ዘመቻ ላይ አውሮፕላኑን በፀረ አውሮፕላን መትተው እንደጣሉ የገለፁ ቢሆንም ጦር ኃይሉ ግን ለአውሮፕላኑ መውደቅ ምክንያቱ ቴክኒካዊ ችግር መሆኑን በመጥቀስ የኃይሉ ምክንያት ውድቅ አድርጎታል።

ነገር ግን በአውሮፕላኑ ውስጥ ምን ያህል ሰዎች እንደነበሩ አሁንም የተገለጸ ነገር የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በፌደራል መንግስትና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ሌሎች የጦር አውሮፕላኖች በክልሉ በቴክኔክ ችግር ምክንያት መውደቃቸው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኩል ሲገለጽ ቆይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የወደቁ የጦር አውሮፕላኖች ምንም እንኳን በቴክኔክ ችግር መወደቃቸው ቢገለጸም የህውሓት ተዋጊዎች ግን ተመተዉ እንደወደቁ ነው የገለጹት፡፡

በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑት ሁሉም ኃይሎች በጅምላ ግድያና በሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተከሰሱ ባሉበት ጊዜ በክልሉ ውጊያ መልሶ እንዳየገረሽ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከፍ ያለ ስጋትን ፈጥሯል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 18 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ