የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ክልል በገበያ ስፍራ ላይ የተደረገውን የአየር ጥቃት አወገዘ

0
136

የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦሬል እና ኮሚሽነር ጄነዝ ሌናርቺች በትግራይ ክልል ተጎጋ በንጽኋን ላይ የደረሰዉን የአየር ጥቃት የሚያወግዝ የጋራ መግለጫ አወጡ፡፡

በጋራ ባወጡት መግለጫ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችው መቐለ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ደጉዓ ተምቤን አቅራቢያ ቶጎጋ በምትባል አካባቢ ማክሰኞ ሰኔ 15፤ 2013ዓ.ም በገበያ ቀን በንጽኋን ዜጎች ላይ የአየር ጥቃት መደረጉን በማረጋገጥ በእጅጉ ኮንኗል፡፡

በቶጎጋ በንጽኋን ላይ የደረሰዉ የአየር ጥቃት የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ህግን የሚጥስ ከመሆኑም በተጨማሪም ቀደም ብሎ ከተስተዋለው ረሀብ፣ ብሄር ተኮር ጥቃት እና ፆታዊ ጥቃትን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም ሁኔታ ጋር ተዳምሮ የሚታይ እንደሆነና የትግራይ ክልልን ጉዳይ አስፈሪ ያደርገዋል ብለዋል።

የአዉሮፓ ህብረት ንጽኋን ዜጎችን ኢላማ የሚያደርጉ ጥቃቶችን እንደሚያወግዝ በመግለጫዉ አስቀምጥዋል፡፡ ይህ ተግባር ኢፍትሀዊና የአለም አቀፍ ህግን የሚጻረር ነው ብሎታል፡፡

የሃገርን ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚል ምክንያት  በንጽኋን ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ በምንም አይነት መልኩ ተቀባይነት እንደሌለዉ ተገልጽዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በመግለጫው አክሎም በቶጎጋ በአየር ጥቃት የተፈጸመባቸዉን ንጽኋን ዜጎች የህክምና እርዳታ የሚሰጡትን አምቡላንሶችን መከልከል ተቀባይነት የለዉም ብለዋል፡፡

እንዲህ አይነት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት የጄኔቫ ስምምነት እና የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግን ይፃረራል ሲል ህብረቱ አሳውቀዋል፡፡፡፡

ሁለቱም የህብረቱ ተወካዮች አሁንም በትግራይ ተኩስ እንዲቆምና የሰብአዊ እርዳታ ካለምንም መገደብ ወደ ክልሉ እንዲደርስ አሁንም አሳሰስበዋል፡፡   

በትግራይ እየተፈጠረ ያለዉ ሁኔታ አስደንጋጭ ነዉ ሲሉ ተወካዮቹ በጋራ መግለጫቸዉ አስታዉሰዋል፡፡ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድም አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያን ጉዳይ በሃምሌ ወር በሚኖረው የህብረቱ  ስብሰባ ላይ በአጀንዳነት እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቶጎጋ በገበያ ላይ በተፈጸመዉ የአየር ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ንጽኋን ዜጎች ሞቷል ያለ ሲሆን ድርጊቱም አዉግዝዋል፡፡ በተጨማሪም የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን ዜጎች የህክምና እርዳታ እንዳያገኙ እየተከለከሉ አንዳለም መረጃ እንደደረሰዉ በቃለ አቀባዩ በኩል አስታዉቅዋል፡፡

ለመንግስት ሀላፊዎችም ለተጎጂዎች አፋጣኝ የህክምና እርዳታ እንዲሰጥ ሚኒስቴሩ አሳስብዋል፡፡

የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቃቱ በገለልተኛ አካል እንዲጣራና ሀላፊነት የሚወስድ አካል መጠየቅ አለበት ሲልም በድረገጹ ገልጽዋል፡፡ ሚኒስቴሩ የዜጎችን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ በትግራይ ተኩስ እንዲቆምና የሰብአዊ እርዳታ ካለ ገደብ እንዲዳረስ አሳስብዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 17 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ