ጆን ማርሽ የምርጫው ልዩ እንግዳ እንጂ ታዛቢ እንዳልነበሩ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

0
69

ትናንት ጠዋት በመኝታ ክፍላቸው ሞተው የተገኙት ጆን ማርሽ የምርጫው ልዩ እንግዳ እንጂ ታዛቢ አለመሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ የካርተር ማዕከልን በመወከል በምርጫው የተገኙ ዓለም አቀፍ ታዛቢ ናቸው መባሉን አስተባብሏል፡፡

የምርጫውንና የቆጠራ ሂደቶችን በማስመልከት መግለጫን የሰጡት የቦርዱ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ሶልያና ሽመልስ “ግለሰቡ በእርግጥ በታዛቢነት ሳይሆን ድጋፍ እንደሚሰጡ እንደ ማንኛውም ዓለም አቀፍ ተቋም በእንግድነት (አስ ኤ ገስት) ነው ከእኛ (ቦርዱ) ባጅ የወሰዱት” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የልዩ እንግዳ ባጅ በተለያየ ሁኔታ የምርጫውን ሂደት የሚከታተሉ ነገር ግን የመታዘብን ስራ የማይሰሩ አካላት ከአጋር ድርጅቶች፣ ከኤምባሲዎች ከመሳሰሉት የሚሰጥ ባጅ ነውም ብለዋል ኮሙኒኬሽን አማካሪዋ፡፡

ስለዚህ ካርተር ማዕከል ታዛቢም የለውም ኢትዮጵያ ውስጥ ለመታዘብም የመጣ ተልዕኮ የላቸውምም ነው ያሉት፡፡

ሆኖም ጆን ማርሽ እንደ ግለሰብ ግን እንደ አንድ ተቋም ድርጅቱን ወክለው የምርጫውን ሂደት ለማየት መምጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኮሙኒኬሽን አማካሪዋ ትናንት በሆቴላቸው ድንገተኛ ሞት እንዳጋጠማቸው ከጸጥታ ኃይሎችና ከፖሊስ ሰምተናል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ይህ ከምርጫው ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለውና በግለሰቡ ሞት እንዳዘኑ ገልጸዋል፡፡

የማዕከሉ የአዲስ አበባ አስተባባሪ መሆናቸው የተነገረላቸው የጆን ማርሽ የአሟሟት ሁኔት ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር እየተጣራ ነው ሲል አል ዐይን ዘግቧል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 15 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ