በምኝታ ክፍሉ ሞቶ የተገኘዉ አሜሪካዊ የምርጫ ታዛቢ ፓሊስ ምርመራ እያደረኩኝ ነው አለ

0
148

በውጭ አገር ታዛቢው የአሟሟት ሁኔታ ላይ ምርምራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ፖሊስ “ትናንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል አሜሪካዊ ዜጋ በመኝታ ክፍሉ ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል” ብሏል።

የሆቴሉ የጽዳት ሠራተኛ ትናንት ጠዋት አንድ ሠዓት ገደማ አሜሪካዊው ያረፈበትን የመኝታ ክፍል ለማጽዳት ስትገባ ያየችውን ነገር ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቷን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ መረጃውን እንዳገኘ ወደ ስፍራው መንቀሳቀሱን እና አሜሪካዊው ከአልጋው ላይ ወደ መሬት ወድቆ ሕይወቱ አልፎ እንደተገኘ አመልክቷል።

በሟች ኪስ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ የምርጫ ታዛቢ ወረቀት (ባጅ) ፣ የተለያዩ መታወቂያዎችና መንጃ ፈቃድ ተገኝቷል።

መንጃ ፈቃዱ “በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ብሔራዊ የድራይቪንግ ላይሰንስ” የሚል እንደሆነ ተገልጿል።

ፖሊስ አሜሪካዊው ሚጠቀምባቸው ‘በርካታ’ መድሃኒቶች ማግኘቱንና “ምናልባት ሁኔታው ሲታይ በተፈጥሮ የሞተ እንደሚመስል ፥ ነገር ግን ትክክለኛው መረጃ ከአስከሬን ምርመራ ውጤት በኋላ የሚታወቅ” መሆኑ አስረድቷል።

በአሜሪካዊው ዜጋ ሰውነት ላይ ምንም አይነት የአካል ጉዳትና ቁስለት አለመገኘቱንም ፖሊስ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን በአሜሪካዊው ዜጋ አሟሟት ላይ ምርምራ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት በቀጣይ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።

የካርተር ሴንተር ፕሮግራም በኢትዮጵያ በይፋዊ የትዊተር ገጹ ባወጣው መረጃ በራዲሰን ብሉ ሆቴል ሕይወቱ ያለፈው የተቋሙ የአዲስ አበባ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ጆን ማርሽ መሆኑን አሳውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 15 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ