ኢብራሂም ሬሲ የኢራንን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ

0
65

ኢራናዊያን በትናንትናው ዕለት ባካሄዱት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የቀድሞው ዳኛ ኢብራሂም ሬሲ ምርጫው አሸንፈዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

እኝህ ተመራጭ ፕሬዘዳንት አሜሪካ በሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት ማዕቀብ ከተጣለባቸው ኢራናዊያን መካከል አንዱ ናቸው።

ተሰናባቹ የኢራን ፕሬዘዳንት ሀሰን ሮሃኒን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት ለኢብራሂም ሬሲ እንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን በማድረስ ላይ መሆናቸውንም ዘገባው ጠቁሟል።

የምርጫው ውጤት ቆጠራው እስካሁን በመካሄድ ላይ ሲሆኑ ዳኛ ኢብራሂም ሬሲ ከወዲሁ ፕሬዘዳንት የሚያደርጋቸውን ድምጽ ማግኘታቸው ታውቋል።

በኢራን በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተሳተፉት መራጮች ጋር ሲነጻጸር 44 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ተገልጿል።

ለአስራ ሦስተኛው ጊዜ በተካሄደው ባለው የኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አራት እጩዎች ተወዳድረዋል።

በዚህ ውስጥ ሦስቱ ከአክራሪ ክንፍ ሲሆኑ አንድ እጩ ደግሞ ለዘብተኛና የመካከል ፖለቲካ የሚራምድ የለውጥ አራማጆች የሚደገፍ ነው፡፡

የኢራን የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን ካለው የመራጮች ተሳትፎ ማነስ የተነሳ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በመጀመርያ ዙር የምርጫ ሂደት ላያልቅ ይችላል የሚል ግምት አስቀምጠው ነበር።

በዚህ ምርጫ ሶስቱን አክራሪ ክንፍ የወከሉት ኢብራሂም ረኢሲ፣ ሙህሲን ሪዳኢ እና አሚር ሂሴን ሲሆኑ አብዱልናስር ደግሞ ለዘብተኛና የመካከል ፖለቲካ ክንፉን ወክለዋል ተብሏል፡፡

በኢራን ምርጫ ህግ መሠረት የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ የሚሆነውና መንበረ ስለጣኑን የሚቆናጠተው ሙሉ ድምጽ ያገኘ ተመራጭ ሲሆን እጩዎቹ በመጀመሪያው ዙር የሚጠበቅባቸውን ድምፅ ካላገኙ ግን ብዙ ድመፅ ያገኙ እጩዎች በሁለተኛው ዙር ይወዳደራሉ::

በፈረንጆቹ ከነሀሴ 2013 ጀምሮ ኢራን በፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሀኒ እየተመራች ያለች ሀገር እንደሆነች ይታወቃል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 12 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ