ታዛቢ ቡድን ባለመላኬ ተጸጽቻለሁ – ተመድ

0
96

የአውሮፓ ህብርት ኢትዮጵያ ሰኔ 14 ቀን 2013 ላይ በምታካሂደው 6ኛ ሃገራዊ ምርጫ ታዛ ቡድን ባለመለኬ ተጸጽቻ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከወር በፊት ህብረቱ ለመታዘብ ያስችሉኛል ባላቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረገው ውይይት አለመስማማቱን ገልጾ፣ የመታዘብ እቅዱን ማንሳቱን አስታውቆ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ህብረቱ ምርጫ 2013 ለታዘብ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች “ሉዓላዊነት ስለሚጋፉ” ስለሆኑ ህብረቱ ምርጫ ለመታዘብ ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታ እንደማይቀበል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አቋሙን ካሳወቀ በኋላ ህብረቱ የምርጫው እለት ልኡክ እንደሚልክ አስታውቆ ነበር፡፡ ህብረቱ በዛሬ መግለጫ በድጋሚ ምርጫውን የሚታዘብ ልዑክ መላክ እንደማይችል እና በድርጊቱ ማዘኑን ገልጿል።

ሰኞ ሰኔ 14 የሚካሄደው ምርጫ ለ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ለውጥ ሂደት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጸው ህብረቱ በቀጣይ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብሮ እንደሚሰራ አስታውቋል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፤የፖለቲካ ውጥረቶች እና ሌሎች ውስብስብ ችግሮች አሉባት ያለው የህብረቱ መግለጫ በቀጣይ ሁሉን አቀፍ እና አሳታፊ ውየይቶች እንዲደረጉም አሳስቧል።

በተጨማሪም ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና እጩ ተወዳዳሪዎች፣ የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ እንዲመቻች ፣ የፕሬስ እና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ እንዲሁም የጋዜጠኞች ድህንንት ፣ የምርጫ ታዛቢዎች ደህንነት እንዲሁም የተሟላ የሎጂስቲክስ እና አስተዳደራዊ ድጋፍ ለምርጫ ቦርዱ በአግባቡ መከናወን እንዳለበት ህብረቱ ባወጣው መግለጫ አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፖለቲካ ሽግግር እረዳለሁ ያለው ህብረቱ የምርጫውን ሂደት እና የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ስራ እንደሚደግፍ ገልጿል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 12 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ