እንግሊዝ ከኢትዮጵያ የዘረፈቻቸውን ቅርሶች ለመሸጥ ያወጣችውን የሀራጅ ጨረታ አገደች

0
58

እንግሊዝ ውስጥ በዛሬው ዕለት ሰኔ 10/2013 ዓ.ም በጨረታ ሊሸጡ የነበሩና ከመቅደላ የተዘረፉ ሁለት ቅርሶች ሽያጭ መቆሙ ተገለጸ።

ጨረታውን ያወጣው የእንግሊዙ በስቢ ኦክሽነርስና ቫሉወርስ የተባለ የጨረታ ድርጅት ሲሆን በእንግሊዝ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር ያደረገው ውይይትን ተከትሎ ነው ጨረታው እንዲንዲቋረጥ የተደረገው።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ በጨረታ ሊሸጡ የነበሩት ቅርሶች ጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱስ ከነ ማኅደሩና መስቀል እንዲሁም ፅዋዎች መሆናቸውን አስታውቋል።

እነዚህ ቅርሶች በመቅደላ ጦርነት ወቅት ዘምተው ከነበሩት የእንግሊዝ ወታደሮች መካከል በጄኔራል ዊልያም አርቡትኖት አማካኝነት የተዘረፉ ናቸው።

በመቅደላ ወቅት የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ እየተደረገ ካለው ጥረት ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለበስቢ ይፋዊ በሆነ ደብዳቤ ቅርሶቹ ከሽያጩ እንዲወጡ የጠየቀው ባለፈው ሳምነት ነበር።

ከዚህም በተጨማሪ ቅርሶቹንም ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበትን ሁኔታ ድርጅቱ እንዲተባበርም ተጠይቋል።

“ከበስቢ ጋር ስምምነት ላይ በመድረሳችን ደስተኞች ነን። እነዚህ ቅርሶች ለኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ባህላዊ፣ መንፈሳዊና ታሪካዊ እሴቶች አሏቸው። የአሁኑም ሆነ መጪው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ቅርሶቻቸውን እንዲጠበቁ ይሻሉ። እናም እነዚህ ብርቅዬ ቅርሶች ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ወቅትም በጉጉት እንጠብቃለን” በማለት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል አቶ በየነ ገብረ መስቀል ተናግረዋል።

ኤምባሲው ቅርሶቹ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበትን ሁኔታም በተመለከተ ከበስቢ ጋርም ውይይቱን እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 10 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ