አቶ ዳውድ በቁም እስር ላይ መሆናቸው አሳስቦኛል – አምነስቲ ኢንተርናሽናል

0
75

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ ከአንድ ወር በላይ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጸ።

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚያዝያ 25፣ 2013 አንስቶ በቤታቸው በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ የጠቆመው አምነስቲ፣ ፖሊስ ቤታቸው ገብቶ ብርበራ በማድረግ ላፕቶፕ እና ስልክ መውሰዱን እንዲሁም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቤታቸው ማንም ሰው ዝር እንዳይል መከልከሉንም አሳውቋል፡፡

አምነስቲ እንዳለው ከሆነ ፖሊስ ይህን ተግባር የፈጸመው ያለምንም ሕጋዊ ማዘዣ በመሆኑ የፖለቲከኛው የመንቀሳቀስ መብት ተጥሷል ነው የተባለው፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በማስመልከት ለሰላም ሚኒስቴር ሙፈሪያት ካሚል ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን፤ በዚህም የአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሕግ ውጪ በቁም አስር ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንዳሳሰበው አመልክቷል።

አምነስቲ በደብዳቤው አሁንም ቢሆን አቶ ዳውድ ኢብሳ በአስቸኳይ ከቁም እስር ነጻ እንዲወጡ የጠየቀ ሲሆን፣ ይህ የማይደረግ ከሆነ ደግሞ በቂ ማስረጃ ካለ ፖሊስ በፖለቲከኛው ላይ ክስ ሊመሠርት እንደሚገባ ነው ያመለከተው፡፡

በተጨማሪም አቶ ዳውድ ምግብ እና ሌሎች የሚፈልጓቸው ነገሮች እንዲቀርብላቸውም አምነስቲ ለወይዘሮ ሙፈሪሃት በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል፡፡

ሊቀ መንበሩ በመጪው ሰኞ በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ እንደማይወዳደሩ ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 09/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ