የሶማሊያ መንግስት የተመድ ሪፖርትን ውድቅ አደረገ

0
142

ሶማሊያ ወታደሮቿ በትግራይ ክልል በተካሄደዉ ጦርነት ላይ ተሳትፈዋል የሚል የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት የሶማሊያ መንግስት ውድቅ አደረገው፡፡

የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የሆኑት ዑስማን ዱቤ የሶማሊያ ወታደሮች በኤርትራ ካምፕ ወታደራዊ ስልጠና ወስደዉ በትግራይ ጦርነት ተሳትፈዋል የሚለዉን መረጃ ወቅሷል፡፡

የወታደሮቹ ቤተሰቦች መንግስት የልጆቻቸዉን ህልዉና እንዲያሳዉቃቸዉ በመቋድሾ አደባባይ ወጥተዉ ድምጻቸዉን ያሰሙ ሲሆን መንግስት መላ እሲከሰጣቸዉ ተቃዉሟቸዉ ማሰማት እንደሚቀጥሉ አሳዉቀዋል ፡፡ 

ዑስማን ዱቤ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የሚወጡ መረጃዎችን መሠረተ ቢስ አሉባልታዎች እና ከፖለቲካ የመነጩ ፕሮፖጋንዳዎች ናቸው ብለዋቸዋል፡፡

የሶማሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያ ይሁን በትግራይ እንዲሁም በአክሱም ግጭት አልተሳተፉም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

የሶማሊያ መንግሥት ምላሹን የሰጠው ከሰሞኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ሰነድ ወደ ኤርትራ ለሥልጠና የሄዱ ወታደሮች በትግራይ ክልል ጦርነት መሳተፋቸውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የወታደሮቹ ቤተሰቦች ለዳግም ተቃውሞ አደባባይ በመውጣታቸው ነው ተብለዋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት በሪፖርቱ ወታደሮቹ በአክሱም ጭፍጨፋ መሳተፋቸውንም ያመለከተ ቢሆንም፣ የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር ግን በየትኛውም የትግራይ አካባቢ ወታደሮቻችን አልተሳተፉም፣ አሁንም የሉም ብለዋል ሲል ቪኦኤ ዘግቧል፡፡

በትላንትናው እለት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳር ዲና ሙፍቲ በነበራቸው ሳምንታዊ መግለጫ የሶማሊያ ወታደሮች በትግራይ ክልል ስለ መሳተፋቸው በጋዜጠኞች የቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡበት ቀርተዋል፡፡

ዑስማን ዱቤ አክለውም ወታደሮቹ ለምን ኤርትራ እንደሄዱ ባብራሩበት ወቅት የሶማሊያን ጦር ለመገንባትና ለማጠናከር እገዛ አንደሚያደርጉልን ወዳጅች ሀገራት ኤርትራም ለወታደሮቻችን ስልጠናዎችን ትሰጥልናለች ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ