የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ መስመር ፍተሻ ተጀመረ

0
68

በቅርቡ የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ ለሚጀምረው የህዳሴ ግድብ የኤልክትሪክ መስመር ዝግጁ እተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

በዚህም የኤልክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታው በተጠናቀቀው የህዳሴ- ደዴሳ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተለያየ ምክንያት የተሰበሩትን ኢንሱሌተሮችን በአዲስ የመተካት ስራ መጀመሩንም አል ዐይን ዘግቧል፡፡

የምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ቶማስ መለሰ፤ ኢንሱሌተሮቹን የመተካት ሥራው የተጀመረው በቅርቡ የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ ለሚጀምረው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መስመሩን ዝግጁ ለማድረግ ነው ብለዋል።

ኢንሱሌተር የመቀየር ሥራው ከህዳሴ- ደዴሳ – ሆለታ ድረስ ከተዘረጋው መስመር መካከል እስከ ዲዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ ባለው በሁለቱም የማስተላለፊያ መስመሮች (ሎት1 እና ሎት 2) በተተከሉ ምሶሶዎች ላይ የሚከናወን መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በመስመሩ ላይ በተካሄደለት የፍተሻ ስራ መሠረት በሁለቱም መስመሮች ላይ ከተተከሉት 1 ሺህ 535 ምሶሶዎች መካከል በ312 ምሶሶዎች ላይ የሚገኙ ኢንሱሌተሮችን በሌላ የመቀየር ስራ እንደሚከናወን ኃላፊው ጠቁመዋል።

በቀጣይ ከደደሳ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ሆለታ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው ባለ 500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተሰበሩ ኢንሱሌተሮችን በተመሳሳይ የመቀየር ሥራ እንደሚከናወንም ጠቁመዋል።

የዲዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ስምንት ባለ 33 እና ሁለት ባለ 132 እንዲሁም አንድ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ በአሁኑ ሠዓት ሁለት ባለ 33 እና አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ለነቀምቴ ከተማ እና አካባቢው ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የህዳሴ ዲዴሳ ሆለታ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ቻይና ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጅ በተሰኘ ኩባንያ መገንባቱ ይታወሳል።

ከ80 በመቶ በላይ ግንባታው የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በያዝነው የክረምት ወራት 18 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ መያዝ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

በነሀሴ 2013 ዓ.ም መጨረሻ ቀናት ሁለት ተርባይኖች 700 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት አንደሚጀምሩ የውሃ፤መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ከዚህ በፊት መናገራቸው ይታወሳል።

የፊታችን ነሀሴ ወር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫት እንደሚጀምሩ መገለጹ ይታወሳል።

ተርባይኖቹ እያንዳንዳቸው 350 ዋጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፤ በድምሩ በቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራው 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ ይሆናል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 04/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

 

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ