በህክምና አቅርቦት እጥረት ሳቢያ የእናቶች ሞት ጨምረዋል – የአክሱም ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል

0
64

በፌደራል መንግስትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) መካከል በተጀመረ ጦርነት ሳብያ በአክሱም በቂ የህክምና አቅርቦት ባለመኖሩ የነፍሰጡር እናቶች ሞት በእጥፍ ጨምረዋል ተባለ፡፡

የአክሱም ሆስፒታል ጦርነቱ ከሚደረግባቸው ገጠራማ አከባቢዎች  ጉዳት ደርሶባቸው  ወደ ሆስፒታል የገቡ ቁስለኞች እያስተናገዱ ነው ሲል ቪኦኤ በዘገባው አስፍረዋል፡፡

ከቪኦኤ ተወክላ የሄደች ጋዜጠኛ በሆስፒታሉ የነበሩ ቁስለኞች ያነጋገረች ሲሆን በጦርነቱ መጀመርያ ላይ ዜጎች ከከተሞች ወደ ገጠር መንደሮች ይፈናቀሉ ነበር ፤ አሁን ላይ ግን ነገሮች ተገለባብጠዉ በገጠር አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ወደ ከተማ እየፈለሱ ይገኛሉ ብላለች፡፡

በጦርነቱ የተነሳ ነፍስጡር እናቶች ወደ ህክምና ማእከል መድረስ ባለመቻላቸዉ የእናቶች ሞት በእጥፍ መጨመሩን የሆስፒታሉ ዳይሬክተር በመጥቀስ ቪኦኤ ዘግቧል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸዉና ህሙማን ወደ ህክምና ማእከል መድረስ አይችሉም፡፡ አብዛኞቹ በትግራይ የሚገኙ ጤና ጣብያዎችና ሆስፒታሎች በጉዳት አልያም በዝርፍያ ምክንያት አገልግሎት ስለማይሰጡ ዜጎች በሚኖሩበት አከባቢው ምንም አይነት የጤና ድጋፍ እያገኙ አይደለም ተብለዋል፡፡

የእናቶች ሞት በእጥፍ ጨምረዋል፤ እኝህ እየሞቱ ያሉት እናቶች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸዉ ሳይሆኑ በምጥና በወሊድ ጊዜ በህክምና እርዳታ እጦት ምክንያት ህይወታቸዉን የሚያጡ ናቸዉ ይላል ቪኦኤ፡፡

ከምግብ አቅርቦት እጥረት በተጨማሪ የመሰረታዊ የምግብ ዋጋ በእጥፍ ጨምርዋል፡፡ በከተማዋ ከፍተኛ የሆነ የዝርፍያ ወንጀል ያለ ሲሆን ሆስፒታሎች ሳይቀሩ ካአንድም ሁለት ጊዜ ተዘርፈዋል፡፡

የአክሱም ሆስፒታል ከጥቂት ወራት በፊት ሙሉ መድሃኒቱ እስኪያልቅ ድረስ የተዘረፈ ሲሆን እስካአሁንም የመድሃኒቶች አቅርቦትን ማሟላት እንዳልተቻለ ነው የተገለጸው፡፡

ጋዜጠኛዋ አገኘሁት ባለችው መረጃ መሰረት አብዛኛው ዝርፍያ እየተፈፀመ ያለው ምስክር በሌሌበትና ሰዎች ከቤታቸው ከራቁ ቡኋላ ነው ትላለች፡፡

የቪኦኤ ጋዜጠኛ ወደ ሓውዜን ተጉዛ እንደነበር ገልጻ በቦታው ሁለት መቶ ሰዎች የተቀበሩበት 20 የወል መቃብሮች ማግኘትዋን ትመሰክራለች፡፡

በአከባቢው ያገኘቻት ለታይ ግርማይ ለቪኦኤ አስከሬኖቹ ወደ ቤተክርስትያን የሚወስድለን ሰው አጥተን ሰባትና ስምንት ቀናት ጎዳና ላይ ከቆዩ በኃላ ጥቂቶቹ ቀበርናቸው ትላለች ፡፡

ለታይ ከተማዋ በከባድ መሳሪያ በመደብደብዋ ህጻናትም ጭምር ሞተዋል፡፡ ሬሳዎች በስብሰው ትል ወጥቶባቸዉ መጥፎ ሽታ ከፈጠሩ በኋላ እንደተቀበሩ ገልጻለች፡፡

የሓውዜን ከተማ ኗሪዎች ከዚህ የባሰ ክስተት አይመጣም ሲሉም ለቮኦኤ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቲር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሰሞኑን በትግራይ ያለዉ የጤና ስርዓትን በሚመለከት በሰጡት መግለጫ ላይ መንግስት የጤና ተቋማቱ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ነዉ ያሉ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ 55 በመቶ የሚሆኑት ሆስፒታሎች እንዲሁም 52 በመቶ የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ማለታቸዉ ይታወቃል።

አገልግሎት በሚሰጡ ሆስፒታሎችም ሆነ የጤና ማዕከላት 95 በመቶ የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች በየቀኑ አገልግሎት መስጠት ቀጥለዋል፤ የቀሩት የጤና ተቋማት ላይ የደረሰባቸው ጉዳት ተግመግሞ መልሰው እንዲቋቋሙና አገልግሎት እንዲጀምሩ ከፌደራል መንግሥት በኩል ለ14 ሆስፒታሎችና 58 የጤና ማዕከላት ገንዘብ ተመድቧል ማለታቸዉ ይታወሳል።

ሚኒስቲርዋ አስፈላጊ የሚባሉ የጤና ቁሳቁስ ግብዓቶች እንደ አልትራ ሳውንድ፣ ቬንትሌተር፣ ማይክሮስኮፖችን ጨምሮ ከ310.8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መድኃኒቶችና ሌሎች ግብዓቶች ወደ ክልሉ መላኩ ተናረዋል፡፡ በአጠቃላይ በክልሉ ለጤና አገልግሎት አስፈላጊ ግብዓቶች 215 ሚሊዮን ብር ተመድቦ አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል ማለታቸዉ ይታወሳል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 04/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ