የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ክልል እየተንቀሳቀሱ ነው – ኦ.ነ.ግ.

0
130

የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ዞኖች እየተንቀሳቀሱ ነው ሲል ኦነግ አስታውቆ ነበር ፤ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ግን  ይህ ሀሰት ነው በማለት ይከራከራል።

ነገር ግን የኦነግ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ውስጥ አሉ ሲሉ  ያስረዳሉ።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ.) ሰሙኑን በተደጋጋሚ በማህበራዊ ድረገጹ ላይ የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ክልል መኖራቸዉን የሚያሳይ መግለጫ አዉጥቷል፡፡

በሀሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን አባይ ጮመን ወረዳ ታጥቀዉ የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ጦር ያሏቸዉ የጸጥታ አካላት በሰዎች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸሙ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

አሁን ደግሞ በደቡብ ኦሮሚያ ቦሮናና ጉጂ ዞኖች በሶስት ወረዳዎች በሊባን ፣ ጉሚ ፣ ኤልደሎና ነገሌ ከተማ የኤርትራ ሊሆኑ የሚችሉ የጦር አባላቶች መስፈራቸዉን ኦ.ነ.ግ. በይፋዊ ገጹ አስታውቀዋል፡፡

ሓምሌ 2012 ዓ.ም ላይ በኦነግ የአመራር አለመግባባትን በመፈጠሩ ተከትሎ በሊቀ መንበሩ አቶ ዳዉድ ኢብሳ በጊዚያዊ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊነት መሰየማቸዉ የሚገልጹት አቶ ለሚ ገመቹን የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል አንዳአንድ ቦታዎች ላይ መታየታቸዉ ማህበረሰቡ እንዳሳወቃቸዉ ይናገራሉ፡፡

እኝህ የኢትዮጵያ መከለከያ ሀይል ደንብ ለብሰዉ ግን የአማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋ መናገር የማይችሉት ታጣቂዎች የትግርኛና አረብኛ ቋንቋ ብቻ እንደሚያወሩ አቶ ለሚ ገመቹ ለደቾ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በሄሊኮፕተር ተጭነዉ የመጡ የኤርትራ ወታሮች በቦረና እንደወረዱ ደቡብ ኦሮሚያ መረጃዉን ሰጥቶናል ይላሉ የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ፡፡

እኝህ የኤርትራ ወታደሮች ባረፉበት አካባቢ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸሙ ነዉ ተብሏል፡፡

ከዛም አልፎ በዘረፋ ላይም እንደተሰማሩና ትልልቅ ተቋማትም ጥበቃ ላይ እየተሰማሩ እንዳለ ዘገባዉ ያሳያል፡፡

ይህንን ጉዳይ በሚመለከት የኦሮሚያ ክልል  የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጌታቸዉ ባልቻ የክልሉን ጸጥታ የማስከበር ስራ የክልሉ ጸጥታ ሀይል፣ ሚልሻ፣ ፖሊስና ልዩ ፖሊስ ከላይ እሰከታች በተቀናጀ ሁኔታ እየሰራ ነዉ ይላሉ፡፡

ከዚህ ዉጭ ክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ከአቅሙ በላይ ሆኖ የሌላን ሀይል እርዳታ የጠየቀበት ሁኔታ የለም ብለዋል፡፡

ስለዚህ ኦነግ ያወጣዉ መግለጫ በመረጃ ያለተደገፈና የክልሉን መንግስት ስም ለማጠልሸት ያለመ ዉንጀላ ነዉ ሲሉ አጣጥለዉታል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የኤርትራ ሰራዊት እንዳለ መረጃ የለንም፣ እርዳታም አልጠየቅንም፣ የሚገባበት ምክንያትም የለም ሲሉ ሀላፊዉ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው የተሰየሙት አቶ ለሚ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ጦሩ ቀደም ሲል በምዕራብ ኦሮሚያ አሁን ደግሞ በደቡብ ኦሮሚያ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ ይህም ከማህበረሰቡ የገኘነዉ መረጃ ያረጋግጥልናል ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፈቲ ዛሬ በነበረው ሳምንታዊ መግለጫ ላይ በኦሮሚያ ክልል የኤርትራ ወታሮች ገብትዋል ስለተባለ ጉዳይ መረጃ የለኝም ሲሉ ለጋዜጠኞች ምልሽ ሰጥተዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 03/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ