የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ለትግራይ የ181 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

0
52

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የ181 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች

ድጋፉ በክልሉ አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 3 ሚሊዮን ዜጎች እንደሚውልም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የምግብ፣ የንጹህ መጠጥ፣ መጠለያ፣ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግቶችን ለማቅረብ እንደሚያስችልም የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለአርሶ አደሮች ዘርና ማዳበሪያን ጨምሮ የግብርና ግብአትን ለማቅረብ ይውላልም ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ድጋፉ ለማኅበራዊና ስነ ልቦናዊ ጫና ማገገሚያ ፕሮግራም እንደሚውልም የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 03/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ