ገሃነምን በትግራይ አየሁት – ሊንሲ አዳሪዮ

0
232

የናሽናል ጂኦግራፊ የፎቶ ጋዜጠኛ ሊንሲ አዳሪዮ የትግራይን ሁኔታ አይታ ከተመለሰች በኋላ በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ ጋሃነም አይቼ አላዉቅም አሁን ግን በትግራይ አየሁ ስትል አጋርታለች፡፡

የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችዉ መቐለ ከተማ ሁሉም ነገር የተረጋጋና ህይወት እየቀጠለች ያለች ይመስላል ሆቴሎች ተከፍተዋል፣ ካፌዎች ስራቸዉን ጀምረዋል፣ እንቅስቃሴም አለ፡፡

ልክ ከተማዋን ለቀህ ትንሽ መጓዝ በጀመርክበት ቅጽበት ላይ ግን የመሬት ላይ ገሀንም ማየት ትጀምራለህ ያለችዉ የናሽናል ጂኦግራፊ የፎቶ ጋዜጠኛ ሊንሲ አዳሪዮ በስካይፒ ከሲ ኤን ኤን ጋር  በነበራት ቆይታ ያየችውን ተናግራለች፡፡

መቐለን ለቀህ ወደ ሌሎች የትግራይ ቦታዎች ጉዞ ስትጀምር መንገዶች ተዘግተዋል፤ በአንዳንድ ቦታዎች በኢትዮጵያ ወታደሮች በሌሎች አካባቢዎች በኤርትራ ወታደሮች በየመንገዱ ፍተሻ አለ ትላለች ሊንሲ፡፡

የፎቶ ጋዜጠኛዋ ሊንሲ አዳሪዮ ወደ አንድ አንድ ቦታዎች ጭራሽኑ የተዘጉና መሄድ የማትችልበት መንገዶች  እንዳሉና እሷም ወደ ሰሜናዊና ደቡባዊ የትግራይ ክፍል ለመሄድ የነበራትን እቅድ እንዳልተሳካ ትናገራለች፡፡

በዚህም ምክንያት ወደ ምእራባዊ የክልሏ ክፍል እንደሄደች ትናገራለች፡፡ በጉብኝትዋም በጣም ልብ የሚሰብሩና የሚያስደነግጡ ታሪኮች እንዳገኘችና በቦታዉ ያለዉ ሁኔታ በካሜራዋ ለማስቀረት መሞከርዋን ትናገራለች፡፡

በናሽናል ጂኦግራፊ የፎቶ ጋዜጠኛ ካሜራ ከተነሱ ፎቶዎች አንዱ የ15 ዓመቷ ሴት ልጁ ፊቷ ላይ በተተኮሰባት ጥይት ምክንያት ሁለቱም አይኖችዋ ያጣችዉን ልጃቸዉ የታቀፉ አባት ፎቶ አንዱ ነዉ፡፡

ሊንሲ በጥይት ፌትዋ ተመታ ሁለት ዓይኖችዋ ስላጣች ወጣት ሴት ስታወራ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ቀናት ተጉዛች ነው ያለችው አሁን ልጅትዋ ያለችበት ሁኔታ ስታብራራ ሙሉ ለሙሉ ማየት አትችልም ነው ያለችው ጋዜጠኛዋ፡፡

የቀዶ ህክምና እየተደረገላት ሲሆን ያላት ስቃይ ከባድ እንደሆነና አባትዋም በጭንቀት ላይ እንደሚገኙ ሊንሲ ትመሰክራለች፡፡

በትግራይ ጦርነት ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት የሚሰጡትን መረጃ ትጋራለች፡፡ ጾታዊ ጥቃት እንደ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ እየዋለ ነዉ ትላለች ሊንሲ፡፡

ለዚህም ማሳያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ተጠቂ መሆንዋን እየነገረቻቸዉ አንሰማም ብለዉ ልጆቿ ፊት በተደጋጋሚ የተደፈረችና  በካሜራዋ ፎቶ ያነሳቻትን እናት ታሳያለች፡፡

ሊንሲ ለአስር ቀናት ዛፍ ላይ ታስራ በካምፑ በነበሩት ወታደሮች የተደፈረችና በ10ኛዉ ቀን ስትነቃ የ12 ዓመት ልጇ እግሯ ስር ተገድሎ ያገኘችዉን ወጣትም ፎቶ በካሜራዋ አስቀርታለች፡፡

ጥቃት የደረሰባቸዉ ንጽኋን ዜጎች የህክምና እርዳታ ለማግኘት እንዲህ በቀላሉ አምቡላንስ ማግኘት አይችሉም፤ የትራንስፖርት አዉቶቢሶችን እንዳይጠቀሙ ገንዘብ የላቸዉም ስለዚህ በእግራቸዉ መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፤ የተዘጉ መንገዶችን ትተዉ ሌላ አማራጭ መንገድ መዉሰድም አለባቸዉ ስትልም ሊንሲ አዳሪዮ በትግራይ ያየችዉን ለሲ ኤን ኤን አጋርታለች፡፡

አውሎ ሚድያ ሰኔ 02/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ