የሶማልያ ወታደሮች በትግራይ ጦርነት ተሳትፈዋል – ተመድ

0
194

የተባበሩት መንግስታት በፊደራል መንግስትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) መካከል በተጀመረ ጦርት የሶማልያ ወታሮች መሳተፋቸው ማረጋገጫ አግኝቻለሁ አለ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ወታሮች ከኤትራ ወታሮች ጎን በመቆም እየተዋጉ ነው ሲው ዘ ናሽናል የተባለው ሚድያ የተመደ ሪፖርት ዋቢ አድርጎ በዘገባው አስፍረዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ዘጋቢ በሞሐመድ ባቢከር የተዘጋጀው ባለ 17 ገጽ ሰነድ ፣ የሶማሊያ ወታደሮች በትግራይ ውስጥ መኖራቸውን ያብራራል – ለቀጣይ ጦርነት እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ለሚሄደው የሰብአዊ ቀውስ ሌላ ገጽታን የሚጨምር ጉዳይ ነው ተብለዋል፡፡

የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ግጭት ተሳትፈዋል ከሚሉ ሪፖርቶች በተጨማሪ የሶማሊያ ወታደሮች በኤርትራ ከሚገኙ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች ወደ ትግራይ ጦር ግንባር እንደዘመቱ ልዩ ዘጋቢው መረጃ እንደተቀበለ ነው የተገለጸው በዘገባው፡፡

በተጨማሪም ካለፈው ህዳር ወር ወዲህ ውጊያው ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በማያዳግም ሁኔታ ተመታ በነበረችው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ በሆነችው በአክሱም ከተማ አቅራቢያ የሶማሊያ ተዋጊዎች መኖራቸውን ተጠቅሳል በሪፖርቱ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርትም የቅድስት ማርያም ሆስፒታል እና የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ዘረፋን ጨምሮ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ውስጥ የፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አመልክቷል፡፡

በኤርትራ በሥልጠና ላይ የነበሩ የሶማሊያ ወታደሮች በአክሱም ጭፍጨፋ ላይ ተሳትፎ እንደነበራቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሪፖርቱ አካትዋል፡፡

በትግራይ ክልል ጦርነት ተሳፈዋል የተባሉት እነዚህ ወታደሮች ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ባይጠቀስም፣ ከነበሩበት የጦር ካምፕ ከኤርትራ ወታደሮች ጋር ባንድነት ወደ ትግራይ ዘልቀዋል ነው የተባለው፡፡

የሶማሊያ ወታደሮች ተሳትፎ አላቸው ከተባለበት የአክሱም ጭፍጨፋ በተጨማሪ በትግራይ ክልል መቀመጫ መቀለ ከተማ መታየታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ይህ በእንደዲህ እንዳለ ተመድ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ በርካታ የሶማሊያ ፖለቲከኞችና ዜጎች በፋርማጆ አስተዳደር ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው፡፡

የሶማሊያ ተፎካካሪ ፓርቲ ዋዳጂር መሪ የሆኑት አብዲራህማን አብዲሻኩር ዋርሳሜ የፋርማጆ መንግስት ወታደሮች ወደ ትግራይ ክልል ጦርነት መላካቸዉ ህጋዊ አይደለም ሲሉ ከሰዋል፡፡ የተፎካካሪ ፓርቲዉ መሪ በተጨማሪም የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስቲር የሆኑት መሓመድ ሃሲን ሮብል የወታደሮቹ ቤተሰቦችን አግኝተዉ በስርአት ሪፖርት ማድረግ አለባቸዉ ብለዋል፡፡

በየካቲት ወር የሶማሊያ መንግስት የሀገሪቷ ወታደሮች በትግራይ ጦርነት አልተሳተፉም ሲል ሲኪድ መቆየቱ የሚታወስ ሆኖ ፤ የሶማሊያ ወታደሮች ወደ ኤርትራ ተልከዉ ስልጠና ወስደዉ በትግራይ ጦርነት እንዲሳተፉ የተደረጉት በትግራይ የተፈጸመዉ ግፍ የሶማሊያ ወታደሮችም ተሳታፊ እንደነበሩ ፕሬዝደንቱ ማሳወቅ አለባቸዉ ብለዋል አብዲሻኩር፡፡

የሀገሪቷ የኦን ላይን ሚድያ የሆነዉ ጋሮዌ ኦን ላይን የሶማሊያ መንግስት በወጣት ድሀ ወታደሮች ህይወት አስይዞ በሚስጥር ስምምነት ፈጽምዋል ሲል በድረገጹ ያስነብባል፡፡  

ሁለት ነባር የሶማሊያ የደህንነትና መረጃ ኤጀንሲዎችም (NISA)በምሲጥር በኤርትራ ሰልጥነዉ ወደ ትግራይ እንዲላኩ የተደረጉ የሶማሊያ ወታደሮችን ጉዳይ ፋርማጆንና በስራ ላይ የሚገኘዉ የደህንነትና መረጃ ኤጀንሲ ሀላፊ የሆኑት ፋሀድ ያሲንን ተጠያቂ አድገዋል፡፡

ነባር የሶማሊያ የድህንነትና መረጃ ኤጀንሲ ኃላፊ የነበሩት አብዱላሂ ዓሊ የሶማሊያን ህዝብ ድምጹ ማሰማት አለበት ያሉ ሲሆን በስልጣን ላይ የሚገኙ የሀገሪቷ ፕሬዝደንት ላይም ጫና እንዲፈጥር ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም ፕሬዝደንት ፋርማጆና የደህንትና መረጃ ኤንጀንሲ ሀላፊ የሆኑት ፋሀድ ወታደሮቹ ያሉበት ሁኔታ ማሳወቅ አለባቸዉ፤ ይህ ብሄራዊ ህልዉና ነዉ ሰዎች ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል አብዱላሂ ዓሊ፡፡

ከሳምንታት በፊት የወታሮቹ ቤተሰቦች በአደባባይ ወጥተዉ የልጆቻቸዉ ህልዉና መንግስት እንዲነግራቸዉ ቢጠይቁም በጸጥታ አካላት እንዲበተኑና ካለመልስ ወደ ቤታቸዉ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊያ ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸዉ እዉቅና ዉጪ በኤርትራ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዲ ተደርጓል፡፡

ይህ ክስተት በድጋሚ እንዳይፈጠር ሀላፊነት የሚወስዱ አካላት በአለምአቀፍ ፍርድ ቤት መጠየቅ አለባቸዉ ፤ በትግራይ ጦርነት እንዲሳተፉ የሶማሊያን ወጣቶች የመለመሉ አከላት በአለም አቀፍ የህግ ማእቀፍ መጠየቅ እንደሚገባ የሀገሪቷ በአመራር ላይ የነበሩ አካላት እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡

አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ በኤርትራ ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ የሶማሊያ ወጣቶችን ህይወት ለመታደግ የፖለቲካ አመራሮች አንዳች ነገር እንዲያረጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

አሁን በትግራይ ጦርነት ላይ መሳተፋቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተረጋግጧል የተባሉትን የሶማሊያ ወታደሮችን በሚመለከት የፌዴራል መንግስቱ እና የሕወሃት ኃይሎች ጦርነት በጀመረ ከጥቂት ሳምንታት ውስጥ በሶማልያ ሚድያዎች ዘገባ ወጥቶ የነበረው ቢሆንም የአገሪቱ ባለሥልጣናት ግን አስተባብለው ነበር።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 02/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ