የሲፋን ክብረወሰን በለተሰንበት ግደይ በሁለት ቀናት ልዩነት ተሰበረ

0
88

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከሁለት ቀናት በፊት ተሰብሮ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን አሻሻለች።

አትሌቷ ሶስት ቀናት እንኳ በቅጡ ያልሞላውን ክብረ ወሰን በአምስት ሰከንድ ነው ያሻሻለችው።

ለተንሰበት ኔዘርላንድ፤ ሄንግሎ ውስጥ የተካሄደውን ውድድር በ29 ዲቂቃ ከ1.03 ሰከንድ በመግባት አጠናቃለች።

ባለፈው እሁድ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እና ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሃሰን ከዚህ ቀደም በአልማዝ አያና ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በ10 ሰከንድ አሻሽላ ክብረ ወሰን ሰብራ ነበር።

ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና በ2016 ኦሊምፒክ ላይ ነበር ክብረ ወሰኑን የያዘችው።

“ክብረ ወሰን እንደምሰብር ጠብቄ ነበር” ብላለች የ23 ዓመቷ ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላ።

“እንደገና ይህንን የዓለም ክብረ ወሰን ለመስበር እሞክራለሁ። ከ29 ደቂቃ በታች ለመግባት እጥራለሁ” ስትል አክላለች።

ለተንሰንበት አሁን የዓለማችን የ5 ሺህ ሜትር እና 10 ሺህ ሜትር የሴቶች ሩጫን ክብረ ወሰን ይዛለች።

ይህንን በማድረግ ከኖርዌይዋ ኢንግሪድ ክሪስቲያንሰን በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ ሯጭ መሆን ችላለች።

ለተንሰንበትን ተከትላ ሁለተኛ የወጣችውን ፅጌ ገብረሰላማን ከአንድ ደቂቃ በላይ በሆነ ሰዓት ነው ቀድማ ውድድሯን የጨረሰችው።

ሲፋን ሀሰን እሁድ ዕለት ከሰበረችው ክብረ ወሰን በፊት በ31ኛው የብራዚል ሪዮ ኦሊምፒክ የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የሩጫ ውድድር ላይ ነበር አልማዝ አያና የዓለም ክብረ ወሰን በማሻሻል ያሸነፈችው።

አልማዝ አያና በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን በ14 ሴከንድ 33 ማይክሮ ሴከንድ ነበር ማሻሻል የቻለችው።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 02/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ