ኤርትራ የባይደንን አስተዳደር ወቀሰች

0
97

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትግራይ ክልል ውስጥ ላለው ጦርነት ላለፉት 20 ዓመታት የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባርን ሲደግፉ የቆየ ያሉትን የአሜሪካ መንግስት አስተዳደር ተጠያቂ አደረገ።

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሚካሄደው ወቅታዊ ጦርነት ኤርትራን ተጠያቂ ማድረጉም መሠረተ ቢስ ነው ሲሉ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳሌህ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኡስማን ሳሌህ ትናንት ሰኞ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በፃፉት እና በምክር ቤቱ በተሰራጨዉ ደብዳቤ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በክልሉ ጣልቃ በመግባት እና በማስፈራራት «ተጨማሪ ግጭትን እና አለመረጋጋትን ያስከትላል» ሲሉ ከሰዋል።

የአሜሪካው የዜና ምንጭ አሶሽየትድ ፕሬስ «በግምት ስድስት ሚሊዮን ሕዝብ ይኖርበት ከነበረዉ የትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት አንድ ሦስተኛውን አካባቢዉን ለቅቆ ሸሽቶአል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ በጦርነቱ እንደተገደሉም ይገመታል።

በአሁኑ ወቅት የመንግሥት ወታደሮች ለበርካታ ግፎች ተጠያቂ ናቸው ከሚባሉት ከጎረቤት ኤርትራ ወታደሮች ጋር በትብብር ላይ ናቸዉ» ሲሉ ጽፏዋል ሲል ዶቸ ቨለ ኤ ኤፍ ፒ ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

አውሎ ሚድያ ሰኔ 01/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ