ኤምቲኤን በኢትዮጵያ የቴሌኮም ጨረታ እንደገና እንደሚሳተፍ አስታወቀ

0
85

በኢትዮጵያ በተካሄደው የመጀመሪያው የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ጨረታ የተሰረዘበት የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን ኩባንያ፣ እንደገና በሚወጣው ጨረታ እንደሚሳተፍ አስታወቀ።

ኩባንያው ባለፈው ሳምንት እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያ ትልቅ የቴሌኮም ገበያ በመሆኗ ዳግም በሚወጣው የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ ይሳተፋል።

የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ (ኢንጂነር)፣ የታጠፈውን የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ ዳግም ለማውጣት ባለሥልጣኑ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የደቡብ አፍሪካው ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ራልፍ ሙፒታ ወደ ኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ መግባት የኤምቲኤን የቆየ ፍላጎትና ግብ መሆኑን ገልጸው፣ በተለይ እንደገና በሚወጣው ጨረታ የኢትዮጵያ መንግሥት የሞባይል ባንኪንግ ሥራን የሚፈቅድ ከሆነ ለኩባንያው ትልቅ ዕድል እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

እንደገና በሚወጣው ጨረታ የፖሊሲ ለውጥ የሚታይ ከሆነ፣ ኩባንያውም በጥብቅ ዲሲፒሊን በመመራት አዲስ በሚሰጠው ዋጋ ላይ እንደሚወስን ገልጸዋል።

የኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ (ኢንጂነር) በበኩላቸው፣ እንደገና በሚወጣው ጨረታ አዳዲስ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ሊቀመጡ እንደሚችሉና ከእነዚህም መካከል በቴሌኮም መሠረተ ልማት ዝርጋታ መሳተፍ ሊፈቀድ እንደሚችል ጠቁመዋል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ባለሥልጣኑ በመጀመሪያ ባወጣው ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ጨረታ ኤምቲኤንና ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለ ጥምረት የተወዳደሩ ሲሆን፣ ከሦስት ሳምንት በፊት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 30/ 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ