ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና ሜ/ጄነራል ገዛኢ አበራን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው አስር አለቃ መሳፍንት የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጠው

0
158

የቀድሞ ጠቅላይ ኢታማዡር ጄኔራል ሰአረ መኮንን እና ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጠበት፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3 ኛ የፀረሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ በያዘው ቀጠሮ በችሎት ተሰይሞ ነው በሙሉ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው፡፡

ተከሳሹ በሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ/ም ጄኔራል ሳአረ መኮንን በዕለቱ የአ/አ ምክትል ከንቲባ ከነበሩት ከአቶ ታከለ ኡማ ጋር ችግኝ ተክለው ከተመለሱ በኀላ 12 ሰአት ገደማ በባህርዳር በዶ/ር አንባቸው ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባ መኖሪያ ቤታቸው በስልክ አመራርነት እየሰጡ ባሉበት ወቅት ወደ ቤታቸው ሊጠይቃቸው ከመጣው ሜ/ጄኔራል ገዛኢ አበራን ጨምሮ በሽጉጥ ተመተው መገደላቸው ይታወሳል፡፡

የአማራ ክልል ህገመንግስትን በሀይል ለማፍረስ የፌዴራል መንግስትን ለመቆጣጠር ለታቀደ እቅድ ለማሳካት ተከሳሹ በግንቦት ወር 2011 ዓ/ም በጎንደር ከተማ ከጄኔራል አሳምነው ፅጌ በመገናኘት ተልኮ ተቀብሎ በወንጀሉ ተሳትፏል ተብሎ በ1996 ዓ/ ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1 ሀናለ 35 /38 እንዲሁም 238 በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተሳትፎ በህገመንግስቱና በህገመንግስታዊ ስርአቱ ላይ በሚፈፀም ወንጀል መከሰሱ ይታወሳል፡፡

ተከሳሹ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን መስጠቱን ተከትሎ ዓቃቢህግ የጄኔራል ሰአረ ባለቤትን ኮነሌል ፅጌ እና የጄኔራል ሰአረ አጃቢዎች አጠቃላይ 7 የሰው ምስክርን እና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ አሰምቶ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ እንዲከላከል በሰጠው ብይን መሰረት የተከሳሹም ሶስት የመከላከያ ምስክር አቅርቦ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በተገቢው ማስተባበል አለመቻሉን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

በዚህ መልኩ መዝገቡን መመርመሩን የገለጸው ፍርድ ቤቱ የዓቃቢህግ ማስረጃ ተከሳሹ ወንጀሉን መፈጸሙ ያረጋገጠ ነው በማለት ጄኔራል ሰአረ መኮንን እና ጓደኛቸውን ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራን መግደሉ ተረጋግጧል ሲል ፍርድ ቤቱ በሙሉ ድምጽ ጥፋተኛ ሲል ፍርድ ሰቷል፡፡

በዚህ መልኩ የተከሳሹን የቅጣት ማቅለያ ለመመልከት ፍርድ ቤቱ ለሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል፡፡

ድሬ ቲዩብ እንደዘገበው አስራለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በግራ ጭንቅላቱ ላይ እና በእግሩ ላይ በደረሰው ጉዳት አንድ አይኑ እይታው ተጋርዶ እያነከሰ ፡የነበረ ሲሆን ችሎቱም ስላመመህ ቁጭ ብለህ ተከታተል ሲል ተቀምጦ ፍርዱን እንዲከታተል አድርጓል ፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 27 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ