እንግሊዝና ኔቶ ከፍተኛ ጾታዊ ጥቃት ባሉባቸው ሃገራት ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ ተስማሙ

0
209

እንግሊዝና ኔቶ ጦርነቱ መሰረት አድርጎ በሴቶች ላይ እየድረሰ ላለው ጾታዊ ጥቃቶች ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ ስምምነት ላይ ደረሱ ሲሉ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልእክተኛ ሎርድ አሕመድ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ከግጭት ጋር የተዛመደ ወሲባዊ ጥቃት በዓለማችን ውስጥ አስጸያፊ እና ተቀባይነት የለውም ሲሉ ነው ሎርድ አሕመድ የገለጹት፡፡

በዚህ ሳምንት የእንግሊዝና የኔቶ ሚኒስትሮች እነዚህን ጭካኔ የተሞላባቸው ወንጀሎች ለመቋቋም አሁንና ለወደፊቱ ተጎጂዎችን እና በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለመጠበቅ እንዲሁም ለመደገፍ የሚያስችል ጠንካራ ስምምነት ተስማምተዋል ነው ያሉት ልዩ መልእክተኛው፡፡

በሌላ በኩል የዩናይትድ ኪንግደም የፓርላማ (House of Lord) አባል የሆኑት ሎርድ ዴቪድ አልተን የኔቶና የእንግሊዝ ስምምነትን እድንቀው በቲዊቴር ገፃቸዉ ላይ እንደጻፉት ከሚኒስትራቸዉ ጥሩ ዜና ተስምቷል ያሉ ሲሆን ግጭትን ተከትሎ በህፃናትና ሴቶች ላይ የሚደርሰዉን ጉዳት የሀገራቸዉ መንግስት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥና እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

ሎርድ ዴቪድ ዩናይትድ ኪንግደም በትግራይ ክልል  በተለይ በህፃናትና ሴቶች ግፍና ጾታዊ ጥቃት ያደረሱትን አካላት ለህግ ያቀርባል ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል ጦርነቱ ተከትሎ በህፃናት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት የዓለማ አቀፍ ሚድያዎች በስፋት ሽፋን እየሰጡት ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ በትግራይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በዳሰሰው ዘለግ ያለ የ ኤ ኤፍ ፒ ዘገባ የህጻናት ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን አትቷል፡፡

በዘገባው የ 17 ዓመቱ ወጣት ሃፍቶም ገብረፃዲቅ በትግራይ ክልል ሓውዜን አቅራብያ የምትገኝ የፍረወይኒ ከተማ ይኖር ነበር፡፡ በመጋቢት ወር ቤታቸው በከባድ መሳርያ ከተመታ  በኋላ ቀኝ እጁንና የግራ እጁ ጣቶች አጥቷል፡፡ “በጣም ተጨንቂያለሁ እንዴት ነው ከአሁን በኋላ መስራት የምችለው” ሲል ሃፍቶም ለሚዲያዉ የደረሰበትን የአካል ጉዳት በተጨማሪ የፈጠረበት ስነልቦናዊ ጫና ገልጽዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞች በድምቀት በሚከበርበት የትንሳኤ በአል ላይ በሓውዜን በሚገኘው ቤታቸው ግቢ ውስጥ በደረሰው የከባድ መሳርያ ጥቃት  ቆስሎ እጁ የተቆረጠው የ 12 ዓመቱ ሃፍቶም ገብሩ በመቐለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ክትትል እየተደረገለት ነው፡፡ የ60 አመት የእድሜ ባለጸጋ አባቱ አቶ ገብሩ ወልደአብርሃ  “ሰሜቴን መግለጽ አልችልም በጣም አዝኛለዉ” ሲሉ የልጃቸዉ ጉዳት የፈጠረባቸዉን መጥፎ ስሜት ይናገራሉ፡፡

ሌላኛዋ የጦርነቱ ተጎጂ ኤ ኤፍ ፒ አግኝቶ ያወራት የ15 ዓመቷ ህጻን አክበረት ታደሰ ስትሆን በዚህ ወቅት በደረሰባት የስነ ልቦና ጉዳት ምክንያት እራሷን መመገብ አትችልም፡፡ ህጻን አክበረት በምትኖርበት ቤት አቅራብያ የተፈጠረው ከፍተኛ የሆነ የመሳርያ ፍንዳታ ምክንያት ተደናግጣ ራስዋን መቆጣጠር በማትችልበት ደረጃ የምትገኝ ስትሆን በአባትዋ ታደሰ ገብረመድህን እና በእህትዋ ፋና በዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል እንክብካቤ እየተደረገላት መሆኑ ኤ ኤፍ ፒ በዘገባው አካትቶታል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 27 / 2013 ዓ.ም 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ