ት.ዴ.ፓ በትግራይ ጊዚያዊ የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት እንዲቋቋምና የኤርትራ ኋይል በተጠና መልኩ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ ጠየቀ

0
252

የትግራይ ዴሚክራሲያዊ ፓርቲ የኤርትራ መንግስት በትግራይ ላይ ዘምቶ ህወሓትን መዉጋቱን አድንቆ አሁን ግን የኤርትራ ኃይል ተፈላጊነት ስለሌለው በተጠና መልኩ ትግራይን ለቆ መውጣት አለበት ሲል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

የትዴፓ መግለጫ የአሜሪካ መንግስትን ያወገዘ ሲሆን የህወሓት አመራር ለ27 ዓመታት ያሰቃየው የትግራይ ህዝብን ነው ብሏል። መላ የኢትዮጵያ ህዝብ የመከራው ገፈት ቀማሽ ቢሆንም ከባዱን ግፍ የተሸከመው የትግራይ ህዝብ ነዉ ይላል ትዴፓ፡፡

አሁን በትግራይ ክልል ለተፈጠረው መከራ ተጠያቂው ለሰላም ሲለመን እምቢ ያለው፣ አንድነትን ጠልቶ እገነጠላለሁ የሚለው፣ በሃገሪቷ የመከላከያ ሰራዊት ላይ “መብረቃዊ” ጦርነት የጀመረው ብቸኛው የትግራይ ህዝብ ጠላት የህወሓት አመራር ነው አለ ትዴፓ በመግለጫዉ፡፡

ትግራይ ውስጥ ያለው የተወሳሰበ ቀውስ በአንድ ሰው ወይም በአንድ ድርጅት በጦር ኃይል ብቻ ሊፈታ የሚችልጉዳይ አይደለም።

ትግራይ ሙሉ በሙሉ በህወሓት አመራር ቁጥጥር ስር ለዓመታት ስለነበረችና ሌሎችፖለቲካዊ ድርጅቶችም በትግራይ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ስላደረገ፣ ሁሉም ተቃዋሚ ድርጅቶች ስፋት ያለውመዋቅር አልነበራቸውም።

እንደ ትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እና ዓረና ያሉ ፓርቲዎች በህዝቡ ዘንድ የተሻለእውቅና ቢኖራቸም ሁሉም ተመሳሳይ ያልዳበረ አቅም ነው ያላቸው ያለው ትዴፓ ይህንን ግዙፍ የህወሓት መዋቅር ለመቆጣጠርና ወደ ለውጡ ኃይል ለመቀየር የሁሉም ድርጅቶች ትብበር ያስፈልጋል ብሏል።

ስለሆነም ትዴፓ የፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩል የሚወከሉበት፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የክልሉ ታዋቂ ሽማግሌዎችና የህዝቡ ተወካዮች፣ እና ምሁራን የሚሳተፉበት ምክር ቤት እንዲቋቋም ዳግም አሳስቧል።

ትዴፓ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሲል በህወሓት ላይ የህግ ማስከበር እርምጃ መወሰዱ ተገቢ መሆኑን አምነው የለውጡን ሂደት የሚደግፉና በትግራይ የሚንቀሳቀሱትን ማለቱ ነው ይላል መግለጫዉ።

ትዴፓ በተጨማሪ ጊዚያዊ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቋቋም ያሳሰበ ሲሆን ፤ ከየዞኑ በህዝብ የተወከሉ፣ታዋቂ ግለሰቦች፣ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶችና የሲቪክ ማኅበራት ያሉበት መማክርት ሸንጎ ቢቋቋምየህዝቡን ምክርና ስሞታ በወቅቱ ለማዳመጥና ለመፍታት፣ ጊዝያዊ መንግስትም ለህዝቡ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይረዳል ብሎም ፓርቲዉ ያምናል።

የመጀመሪያው የኤርትራ ኃይል እያደረሰ ባለው ጉዳት ላይ ሲሆን የኤርትራ መንግስት በህወሓት ጁንታ ጥቃት የደረሰበትን የሰሜን እዝ ሰራዊት እንደገና ተደራጅቶ ጁንታውን እንዲመታ በማድረግና የራሱንም ሰራዊት በማሰለፍ ጁንታውን በመጠራረግ ላይ ያደረገውን እርዳታና መስዋእትነት ከፍተኛ ቢሆንም ከዚህ ወዲያ ግንየኤርትራ ኃይል ተፈላጊነት ስለሌለው በተጠና መልኩ ትግራይን ለቆ መውጣት አለበት ነው ያለው።

ይህም ሆኖ የኤርትራ ሰራዊት ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል፣ ንብረት በማውደም እና በመዝረፍ፣ ሴቶችንበመድፈር ያሳየውን አስነዋሪ የሰብዓዊ መብትና የስርዓት ጥሰት አስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ በጥፋተኞች ላይተገቢ ቅጣት እንዲደረግና ለተጎጂዎችም ተገቢ ካሳ እንዲከፈል፣ የዚህ ዓይነት የስነ-ምግባር ጥሰት እንዳይደገምም መንግስት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ትዴፓ በድጋሜ አሳስባለዉ ብሏል።

ትዴፓ የወልቃይትና የራያ የማንነት ጥያቄ በህገ-መንግስቱ መሰረትና በህዝቡ ምርጫ የሚወሰን ጉዳይ ነው ብሎ እንደሚያምን ያሳወቀ ሲሆን መንግስትንም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉትን እርምጃዎች እንዲወስድ ሳሳስብቆይቻለሁ ነው ያለው።

ይህ እስከሚሆን ድረስ ግን አሁን ባለው ሁኔታ የወልቃይትና የራያ ህዝብ እንደ ሌላው የትግራይ ህዝብየራሱን ጊዚያዊ አመራር መርጦ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስር መቆየት ይኖርበታል ፤ ህዝቡና መሬቱ የትም ስለማይሄድና ህዝቡም የራሱን አስተዳደር እስከመረጠ ድረስ፣ ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ሲባል በጥድፊያና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ውሳኔ መደረግ የለበትም ሲል ፓርቲው ገልጿል።

የትዴፓ መግለጫ የአሜሪካ መንግስትን ያወገዘ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት ህዝቡን ለመርዳት የተሰማሩትን ሰዎች እያደፈጠ የሚገድለውን ሽብርተኛው ተላላኪው የህወሓት አመራር ጎን ወግኖ በለውጡ መንግስትና በአገራችን ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ በድርድር ወደ ስልጣን ሊያመጣው ማቀዱ ሊወገዝ የሚገባው ኢፍትሃዊ አሰራር ነው ሲልም በመግለጫዉ አስቀምጧል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 24 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ