በትግራይ በጦርነት ምክንያት ከ 6 ሺህ በላይ ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል ተብለ

0
88

በፌደራል መንግስትና ህዝባዊ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) በተጀመረ ጦርነት ምክንያት ከ6 ሺህ በላይ ህፃናት ከ ወላጆቻቸው ተለያይተዋል ሲሉ የዩኒሴፍ/UNICEF/ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሄንሪታ ፎር አስታወቁ፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሄንሪታ ፎር ፣ የትግራይ ክልል ህፃናት ያሉበት ሁኔታን በተመለከተ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በመግለጫቸው ፣ በትግራይ ጦርነት ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሰባት ወራት በህፃናት ላይ እየተፈፀመ ያለው የመብት ጥሰት መጠን የመቀነስ ምልክት የለውም ብለዋል፡፡

ጦርነቱን ተከትሎ “ከ 6,000 በላይ ሕፃናት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል” ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡ አሁንም ቢሆን ተደራሽ ባልሆኑ የተለያዩ አከባቢዎች ድጋፍ የሚፈልጉ ብዙ ልጆች ይኖራሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው አስረድቷል፡፡

“ሴቶች እና ልጃገረዶች አሁንም ድረስ ለአስፈሪ የፆታ ጥቃት እየተዳረጉ ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፣ “ውጊያው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ለጥቃት ከተጋለጡት 540 በላይ ሴቶች በዩኒሴፍ እርዳታ አግኝተዋል ፤ ነገር ግን በደህንነት እጦትና የበቀል እርምጃን በመፍራት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ተጠቂዎች አስፈላጊውን እንክብካቤና አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ ሆኗል” ሲሉም አክለው ገልጸዋል፡፡

ሄንሪታ ፎር “ልጆች ፣ ወላጆች እና እርዳታ ሰጪዎች በበቀል ስሜት ጥቃት እንዳይደርስባቸው ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ናቸው”ም ነው ያሉት፡፡ በየጊዜው ከዩኒሴፍ አጋሮች የሚደርሳቸው ሪፖርት ይህንን የሚያጠናክር መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በትግራይ ክልል 1.6 ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል የሚሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ከነዚህም ከ 720,000 በላይ ሕፃናት መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ መጠለያ ጣብያዎችና የስደተኞች ካምፖች መጨናነቃቸውን እንዲሁም ከንጽህና መጠበቅ፣ ፆታዊ ጥቃት እና ውሃ ወለድ በሽታዎች ጋር በተያያዘ ጉድለቶች እንዳሉም ነው የዩኒሴፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ ያነሱት፡፡

ሄንሪታ ፎር “አብዛኛው የትግራይ አካባቢ ለሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ተደራሽ አልሆነም” ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡ አክለውም ፣ ከሚያዝያ ወር መጀመሪያ አንስቶ በዩኒሴፍ እና በአጋር ድርጅቶች የተደገፉ በተንቀሳቃሽ ጤና ፣ በምግብ እና የውሃ አቅርቦት ላይ የሚሰሩ ቢያንስ 31 ተልዕኮዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት መተላለፊያ እንዳያገኙ ተደርገዋል” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ በተለያዩ ጊዜያት በሰጠው መግለጫ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ሰጪ ተቋማት እና ግለሰቦች በትግራይ ክልል እርዳታ ለማዳረስ የማያስችላቸው ምንም አይነት ችግር እንደሌለ ሲገልፅ ቆይቷል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 24 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ