ሳወት ትግራይን ሀገር አደርጎ በመፍጠር ጥቅማችንን ማስከበር ይቻላል ሲል ዓረና ትግራይ ደግሞ ተፋላሚ ሀይሎች ጦርነቱን አቁመው ድርድር ይካሔድ አለ

0
169

የትግራይ ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትግራይን በተመለከተ የተለያዩ ውሳኔዎችንና አቋማቸውን ይፋ አድርገል። ፓርቲዎቹ ከሰሞኑ ባደረጉት የየግል ስምብሰባና በሰጡት የተናጥል መግለጫ ነው አቋማችው ያሳወቁት።

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ብሄራዊ አመራር የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታን በማስመልከት ለአራት ቀናት በመቀለ ከተማ ተሰብስቧል፡፡

ፓርቲው የትግራይን መጻኢ እድልና የፓርቲዉ ሁኔታ አስመልክቶ በመገምገም መግለጫ ያወጣ ሲሆን ፤ የፓርቲዉ የአደረጃጀትና አቅም ግንባታ ሀላፊ አቶ ዓብለሎም ገ/ሚካኤል እንደተናገሩት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለዉ ጦርነት ጠቅላላ ጦርነት ብለዉ ያምናሉ፤ ይጠሩታልም።

በሌሎች የአለም ማህበረሰብ በሁለት ሀገራት መሀል በታጠቁ ሀይሎች የሚደረግ ጦርነት የተለመደ ጦርነት ሲሆን በትግራይ ያለዉ ግን ከዚህ የተለየ ጠቅላላ ጦርነት ነዉ፤ ይህም ንጽኃን ዜጎች ይገደላሉ፣ ጾታዊ ጥቃት ይፈጽማ፣ ህንጻዎች ይወድማሉ ብለዋል።

ሆን ተብሎ ወደ ከተማን ላይ ከባድ መሳሪያ ይተኮሳል፣ የእምነት ተቋማት ይቃጠላሉ ፣ ይደበደባሉ፣ የእርሻ መሳሪያዎች ይሰበራሉ ይቃጠላሉ ፤ የመንግስትና የግል ንብረት ይዘረፋል የቀረዉም እንዲወድም ይደረጋል ብሏል አቶ ዓብለሎም፡፡

ፓርቲዉ በመግለጫዉ የትግራይ ጥቅም በሳልሳይ ወያነ ትግራይ መርሆች መነፅር መርምሪያለሁ ያለ ሲሆን ይህ ጥቅም በኢትዮጵያ በማንኛዉም የመንግስት ቅርፅና መዋቅር አይረጋገጥም ብሏል፡፡

በዚህ ወቅት ሁሉም በቻለዉ አቅም ትግራይን ለማምበርከክና ለማጥፋት ዘምቷል ያሉት የፓርቲዉ የአደረጃጀትና አቅም ግንባታ ሀላፊዉ እንደመነሻ የነበረዉ ብሄራዊ ቃልኪዳን ተጥሷል፣ ከዛም አልፎ ፈርሷል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ይህ ማለት የሀገሪቷ የፈደሬሽን ግንባታ በኢትዮጵያ ፈርሷል ማለት ይቻላል ብለዋል ሀላፊዉ ከቪኦኤ ጋር በነበራቸዉ የገለፁ ሲሆን ፤ ፓርቲያቸዉ ኢትዮጵያ ተስፋ አላት ብለዉ እንደማያምንና በሀገሪቷ ተስፋ እንደቆረጡ ገልፀዋል፡፡

በዚህም የፓርቲዉ አመራር የትግራይ ጥቅሞች ሊሳኩ የሚችሉት ነፃና ሉአላዊት የሆነች ሀገረ ትግራይ በመፍጠር ነዉ ሲል በስብሰባዉ ገምግሟል ነው ያሉት።

ነገር ግን እቺ ነፃና ሉአላዊት የምትባለዉ ሀገረ ትግራይ የትግራይን ህዝብ እድል የመወሰን ጉዳይ ስለሚጠበቅባት ከብዙ ሰዎች ጋር መወያየት፣ መነጋገርና ዝርዝር ጥረትም ስለሚያስፈልገዉ ፓርቲዉ ዝርዝር ነጥቦች ከመስጠት ተቆጥቧል ብለዋል።

በሌላ በኩል የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫያውጣው ዓረና ፓርቲ ነው።

 ዓረና ለሉአላዊነትና ዲሞክራሲ ፓርቲም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ ፓርቲዉ በትግራይ ያለዉ ጦርነት ቶሎ ካልቆመ ሁኔታዉ ለሀገሪቷና ለምስራቅ አፍሪካ አደገኛ በመሆኑ ጦርነቱ ቆሞ ተፋላሚ ሀይሎች ወደ ድርድር መግባት አለባቸዉ ብሏል፡፡

ዓረና ፓርቲዎች በሽብርተኝነት መፈረጅም የፖለቲካ ምህዳር የሚያጠብ ህዝብ በጅምላ እንዲታሰር የሚያደርግ በመሆኑ መንግስት ዉሳኔዉን ዳግም ሊያጤነዉ ይገባል ሲል በመግለጫዉ አስፍሯል፡፡

የትግራይ አርሶአደር መሬቱ እንዳያርስ በመከልከል በረሀብ ህዝቡ ለማፅዳት በሚል እቅድ እየተሰራ ነዉ፤ ለእርሻዉ የሚጠቀምባቸዉ ከብቶቹ በማረድ የእርሻ መሳሪያዎቹ እየተቃጠሉና እየተዘረፉ ይገኛሉ ፤ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እንዳያገኝም እየተሰራ ነዉ ብለዋል ዓረና በመግለጫዉ፡፡

ስለዚህም ይህ ተስተካክሎ ህዝቡ ወደ ስራ ሊገባ ይገባል ያለው ፓርቲው ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ከ5.2 ሚልዮን በላይ ህዝብ የምግብ እርዳታ በሚገባ ሊደርሰዉ ይገባል ሲል አሳስቧል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 24 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ