ከሽረ ከተማ ስደተኞች ማእከል ታፍኖ የተወሰዱት ስደተኞች መመለሳቸው ተሰማ

0
86

በትግራይ ክልል ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ከተፈናቃዮች ማቆያዎች በወታደር ታፍኖ ተወሰዱ የተባሉ ሰዎች መመለሳቸው ተገለጸ፡፡

ስደተኞቹ በኢትዮጵያና በኤርትራ ወታደሮች ታፍነዉ መወሰዳቸውንና ድብደባም ተፈጽሞብናል ብለዋል፡፡

ከግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ሰኞ ምሽት ጀምሮ በትግራይ ክልል፤ ሽረ ከተማ ከሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው የመጠልያ ካምፖች ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱ በርካታ ተፈናቃዮች ለሶስት ቀናት ከታፈኑ በኃላ መለቀቃቸው ስማቸው መጥቀስ ያለፈለጉ ስደተኞች ተናግረዋል፡፡

ስደተኞቹ ከፅሀየና ዓዲንፊቶ ከተባሉ ት/ቤቶች እንዲሁም የተፈናቃዮች ማእከላት በወታደሮች ከተወሰዱ ብኃላ ከከተማዋ ወጣ ብሎ ወደ ዓዲ ዳዕሮ የሚባል ከተማ በሚወስድ መንገድ ጉና በተባለ አዳራሽ እንደቆዩ ነው ስደተኘቹ የገለጹት፡፡

ስደተኞች እንደሚሉት ከሆነ ደረታቸውንና ጀርባቸው በዱላ በደረሰባቸው ድብደባ ተጎድተዉ አሁን ተኝተዉ እንዳሉ የገለጹት አንድ አሰተያያታቸው ለ ቪኦኤ የሰጡት ስደተኛ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ማእከሉ እንዲገቡ ባይፈቀድም ወታደሮቹ ግን ይህንን ህግ ጥሰዉ በጨለማ ገብቶ አፍኖ ወስዶናል ብለዋል፡፡

ማታ ሶስት ሰአት አካባቢ ወደ አጠለልንበት ቦታ መጥተዉ በበትር እየደበደቡ ከመጠለያዉ ካስወጡን በኃላ በግራና በቀኝ እንዲሁም ከኋላ በስናይፐር አጅበዉ ነበር  ጉና ወደ ተባለዉ አዳራሽ የወሰዱን፤ በአዳራሹ  ለሶሰት ቀናት ነው የቆየነው፡፡  በ 17 ቀን 2013 ደግሞ ምልሻ ነበርክ የጦር መሳርያህ የታለ እያሉ መደብደብ ጀመሩ ሲሉ ስደተኛው በቦታው የነበረ ሁኔታ ይገልጻሉ፡፡

በዱላ ጆሯቸው ላይ ተመተዉ እየታከሙ እንደሆኑ የገለጹት ሌላኛው ስደተኛ በቦኩላቸው ሶስት ቀን ታፍነዉ ከተለቀቁ ብኃላ በተፈናቃዮች ማዕከላት የነበሩት ስደተኞች በስጋት ወደ ኗዋሪው ህዝብና ወደ ገጠር ሸሽቶ ነው የጠበቁን ብለዋል፡፡

ታፍኖ የነበሩ 204 መሆኑን የገጹት እስካሁን አራት ሰዎች አልተመለሱም ብሎ እንደሚያምኑ ነው የገለጹት ፤ ሁለቱም ታፍኖ የነበሩት ስደተኞች በቀጣይም ስጋት እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡

ስጋት አለን አሁን የምግብ ጉዳይ ሳይሆን እያሳሰበን ያለው የመታፍን ጉዳይ ነው በጣም እያሳሰበን ያለው ወደ ሱዳን ለመሰደድም ለቀይ መስቀል አሳውቀን ገና ምላሽ አላገኘንም ብለዋል ስደተኛው፡፡

እኛ ስንታፈን ብዙ ስለነበርን ይፋ ወጥተዋል፤በቦታ ቢያነስ ሁለት ሶስት ሰዎች በየቀኑ ይታፈናሉ ብለዋል፡፡

ይህንን ጉዳይ በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሙሽን በሽረ ከተማ ከሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው የመጠልያ ካምፖች ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱ በርካታ ተፈናቃዮች ስላሉበት ሁኔታ ክትትል በማድረግ ላይ ነኝ ሲል ከትላንትና ወድያ ባወጣው መግለጫ ገልጸዋል፡፡

በመጠለያዎች የሚወስዱ ማናቸውም የሕግ ማስከበር እርምጃዎችን ሆነ በመጠለያዎቹ ይገኛሉ ተብሎ የሚታሰቡ ተጠርጣሪዎችን የመያዝ እርምጃ ተገቢውን የህግ ሂደት የተከተለና በመጠለያዎቹ እና ተፈናቃዮችን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል ኮሚሽኑ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የስቪል ሰዎች ድህንነትና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውም አይነት ተግባራት አወግዛለሁ ብለዋል፤ አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድም አሳስበዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 21 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ