ነገ የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ጫናን የሚቃወም ሰልፍ ሊካሄድ ነው

0
57

ነገ የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ጫናን የሚቃወም ሰልፍ “ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል መሪ ቃል በመላው ሀገሪቱ ሊካሄድ ነው።

ሰልፉ የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና የሚያሳድሩትን ጫና በመቃወም የሚከናወን ነው ተብሏል።

የአሜሪካ መንግስት ከሰሞኑ የጉዞ እገዳ መጣሉ ይታወሳል።

እገዳው በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረው ጫና ሀገሪቱ ከድህነት እንዳትላቀቅ ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ ነው ያሉት የሰልፉ አዘጋጆች ወጣቶች ለሀገር እድገት የበኩላቸውን በመወጣት የውጭ ጫናን መቃወም ይገባቸዋል ብለዋል።

ወቅቱ ህዝቡ አንድነቱን ይበልጥ ሊያጠናክር የሚገባበት ነውም ነው የተባለው።

ከምዕራባውያን ጫና ለመላቀቅ መስራት በትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባም ተገልጿል።

መርሐግብሩ ነገ እሑድ ግንቦት 22 ቀን 2013 ዓ/ም በመላ ሀገሪቱ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚካሄድ ኢቢሲ ዘግቧል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 21 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ