መጅሊሱ በሚጠበቅበት ደረጃ ችግሮችን ባለመፍታቱ ሀገርና ህዝበ ሙስሊሙን እየጎዳ ይገኛል ተባለ

0
87

መጅሊሱ በሚጠበቅበት ቁመና ላይ ባለመሆኑ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ብሎም ሀገርን በእጅጉ እየጎዳ ይገኛል ሲል በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት የሥራ አመራር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚመጥነው፤ አንድነቱን ሚያጠናክርለት፤የሚወክለው፤ የሚታገለው ሳይሆን የሚታገልለት መሪ ተቋም የረዥም ጊዜ ህልሙ ለማሳካት በጣም ወሳኝ የትግል ግዚያት አልፏል፤ እልፍ አእላፍ መስእዋትነት ተክፈሎበታል ይላል መግለጫው፡፡

የህልውና ጉዳይ የሆነው የመጅሊሱ ተቋማዊ ግንበታ አደጋ ላይ የወደቀ በመሆኑ ጉዳዩን የእስልምና እምነት ተከታዮች በቅርበት በመከታተል በሱፈ-ሰለፊ ማደናገሪያዎች ሳይጭበረበር፤ ለከፋፈዮች ጆሮ ሳይሰጥ በአንድነት እንዲጸና ቦርዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ቦርዱ ከህዝብ የተሰጠውን እምነት ከዳር ለማድረስ እስከ መጨረሻው በጽናት ይታገላል ብሏል ሲል በሰጠው መግለጫዉ አስታውቋል፡፡

የጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔዎች አሁን ባለው ሁኔታ በመቀጠል በአፋጣኝ ተግባራዊ የማይሆኑ ከሆነ በድጋሚ አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሳበ ተጠርቶ ሌላ ተገቢ ውሳኔ እንዲሰጥበት ቦርዱ እንደ አማራጭ እያጤነ የሚገኝ ሲሆን ራሳቸውን ከህዝብ በላይ አድረገው ህዝቡን በመናቅ ውሳኔዎቹ ተግባራዊ እንዳይሆኑ እየሰሩ ያሉ ግለሰቦች ወደ ህሊናቸው ተመልሰው ራሳቸውን እንዲመለከቱ የመጨረሻ ጥሪ ቦርዱ ይሰጣል ሲል አሳስቧል፡፡

በመንግስት በኩል እስከ አሁን የተደረገ ሰፊ ጥረት ቢኖርም ከውጤት አንጻር ሲመዘን ችግሩን ለመፍታት እና የሀገርን ሰላም ለማረጋገጥ የመንግስት እርምጃ ይህ ብቻ ነው የሚል እምነት የሌለን በመሆኑ ጉዳዩ ወደማይፈለግ አቅጣጫ እንዳይሄድ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ግልጽ እና መፍትሄ ሰጪ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት ተነግረዋል፡፡

መግለጫዉ ጉዳዩን የሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ ግንዛቤ ከመፍጠር አንስቶ ሌሎች እውነታዎችን ለሚመለከታቸው እንዲያሳዉቁና የሚጠበቅባቸዉን ሚና እንዲወጡ ጠይቋል፡፡

በመጨረሻም ቦርዱ ከህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ በዚህች ሀገር ላይ የሚደረገውን ኢፍትሃዊ ጫና እንደሚያወግዝና ቀጣይ ሀገራዊ ምርጫም እንዲሳካ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተለይም ሙስሊሙ ህብረተሰብ የበኩሉን እሰተዋጽኦ እንዲያደረግ ጥሪዉን አስተላልፏ፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 20 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ