እናት ፓርቲ አባሎቼና አመራሮቼ ከመንግስት የግድያ ማስፈራሪያና እስር እየደረሰባቸው ነው አለ

0
67

እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ፓርቲው በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ስር በሚገኙ ምርጫ ክልሎች በምርጫ ሂደት ፣ በዕጩዎች እና አባሎቹ ላይ ችግር እየደረሰብን ነው ብለዋል፡፡

ፓርቲው ደርሰውብኛል ያላቸው ችግሮች ማስፈራርት፣ በሽጉጥ የመግደል ሙከራ ማድረግ፣ እስር ፣ዕጩዎች ላይ ክትትል የማድረግ ትእዛዝ መስጠት፣ ባነር እና ማስታወቂያዎች መገንጠል፣ በገጠር ቀበሌ ህዝብን እየሰበሰቡ የፓርቲው ስም እንዲጠፋ የማድረግ፣ ስድብ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል ፓርቲው።

ፓርቲ ባወጣው መግለጫ እንደሚያስረዳው ከሆነ ፓርቲው አጋጠመኝ ያላቸው ችግሮች በአማራ ፣ በደቡብ ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ ሐረር ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ነው።

በአማራ ክልል የምርጫ ክልል ውስጥ የብልፅግና አባላት ሕዝቡ ብልፅግናን እንዲመርጥ በቃለ ጉባኤ ማስፈረም፤ የብልጽግና የምርጫ ምልክቱን ቤተ እምነት በር መለጠፍ፣ በሴክተር መሥሪያ ቤት የተወዳዳሪዎችን ፎቶ ግራፍ መለጠፍ፣ በየቀጠናዉ የእናት ፓርቲ የምርጫ ምልክት መቅደድ ይገኙበታል፡፡

ገዥው ፓርቲ ቢቀር የሚቀረው ስልጣን እንጂ የሕይወት ፍጻሜ አለመሆኑን ተረድቶ፣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የወጡ ወጣቶችን በአፈሙዝ እየተገለገሉ ለማስፈራራት መሞከር ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪ ተገባር መሆኑን ተረድተው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን ብለዋል ፓርቲው፡፡

የተለያዩየፖለቲካፐርቲዎች ለምርጫው የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በገዥው ፓርቲ ብልፅግናና በመንግሰት ሰዎች ከፍተኛ ችግር እየደረሰብን ነው እያሉ ነው።

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሲሆን 127 አባላትና ደጋፊዎቹ በኮንሶ ዞን እንደታሰሩበት አስታውቋል።

ፓርቲዉ ቅስቀሳ በሚያደርግባቸዉ የተለያዩ አካባቢዎች ከቅስቀሳ በኋላ አባላትና ደጋፊዎቹ ለእስርና ወከባ እየተዳረጉት መሆኑን ተናግሯል፡፡

በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጸዉ ኢዜማ፣የምርጫ ቅስቀሳዉ ከተካሄደ በኋላ አባላትና ደጋፊዎቹ ለእስርና ወከባ እንደሚዳረጉ የፓርቲዉ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ዘላለም ወርቅአገኘሁ ተናግረዋል ።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 19 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ