በሽረ ከተማ በወታደሮች ተወሰዱ ስለተባሉ ስደተኞች እየተከታተልኩ ነው – ኢሰመኮ

0
69

የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰኞ ዕለት ምሽት በትግራይ ሰሜናዊ ክልል ሽረ ከተማ በአራት ካምፖች የነበሩ ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሚሆኑ ወጣት ሴቶችና ወንዶች በግዳጅ መያዛቸው ሶስት የእርዳታ ሰራተኞች እና አንድ ዶክተር ለሮይተርስ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ክልል፤ ሽረ ከተማ ከሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው የመጠልያ ካምፖች ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱ በርካታ ተፈናቃዮች ስላሉበት ሁኔታ ክትትል በማድረግ ላይ ነኝ ብለዋል፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሐኪሙ በቦታው የነበሩ የአይን ምስክሮችን ቃል በመጥቀስ ብዙ ወጣቶች እንደተወሰዱ ነው የተናገሩት፡፡

ከእርዳታ ሰጪ ሠራተኞች መካከል አንዱ እንዳሉት ከሆነ በርካታ ወንዶች ተደብድበዋል ፣ ስልካቸው እና ገንዘባቸው ተወስዷል ነው ያሉት፡፡

ኢሰመኮ እነዚህ መጠለያዎች መደበኛ መኖሪያ ቦታቸው ያለውን የደህንነት ስጋት ሸሽተው የመጡ ሰዎች ብቸኛ የድህንነት ቦታዎች ሲሆን፤ የሰብአዊ አቅርቦት ፍላጎት አሁንም ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም፤ በእነዚህ መጠለያዎች የሚወስዱ ማናቸውም የሕግ ማስከበር እርምጃዎችን ሆነ በመጠለያዎቹ ይገኛሉ ተብሎ የሚታሰቡ ተጠርጣሪዎችን የመያዝ እርምጃ ተገቢውን የህግ ሂደት የተከተለና በመጠለያዎቹ እና ተፈናቃዮችን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ኢሰመኮ የስቪል ሰዎች ድህንነትና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውም አይነት ተግባራት አወግዛለሁ ብለዋል፤ አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድም አሳስበዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሃገር ውስጥ ተፈናቀዮችና መጠልያ ቦታዎቻቸው በማነኛውም ግዚ ቢሆን ጥበቃ ሊደርግባቸው እንደሚገባ አጽኖኦት ሰጥተዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 19 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ