ቅዱስ ሲኖዶሱ የዛሬ 30 ዓመት የነበረዉን ዓይነት አሰራር ዘርግቶ ቢሰራ ሰዉን ከረሀብና እልቂት ማዳን ይቻላል አለ

0
166

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገዳማትና አድባራት ዲያቆናትና ወጣቶች ምእመናንና ምእመናት ፈተና ላይ ሲወድቁና መከራ ሲጸናባቸዉ ቅዱስ ሲኖዶሱን በቀጥታ ስለሚመለከታቸዉ የመፍትሄዉ አካል ሆኖ መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህንን የፈተና ጊዜ አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን በዝምታ የምናልፈዉ ከሆነ ለቤተክርስትያናችን ታሪክ ጠባሳ መሆኑን አይቀርም ብለዋል አቡነ ማትያስ፡፡ ይህም አማኞች በቤተክርስትያንዋ እምነት እንዲያጡ የሚያደርግ ነዉ ተብለዋል፡፡

ይህ ጉባኤ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተጎዱ የሚገኙት ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም በአጠቃላይ ያለ ፍትህ እየተጎዱ ለሚገኙት ሰዎች የመፍትሄ አምጪ አካል ሆኖ ከጎናቸዉ ሊቆም እንደሚገባ ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስ ገልጸዋል፡፡

ዋስትና ያለው ሰላም በሀገሪቱ ሊረጋገጥ የሚችለው ሀሉም ባለ ድርሻ አካላት በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰብስበው መወያየት ፣ መግባባትና ሀገራዊ ስምምነት መድረስ ሲችሉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሀገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ጉባኤው በጸሎት፣ በማስታረቅ፣ በቁሳቁስና በመጠለያ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ድጋፍ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

አሁን ያለዉ የሀገሪቷ ሁኔታ እንደ እምነት ተቋም መሸሽ ሳይሆን የቤተክርስትያኗ የዉስጥ አቅምን በማየት የምእመናን ትብብርና እገዛ በመጠየቅ እንዲሁም የዓለም አብያተ ክርስትያናትና በጎ አድራጎት ድርጅትን በማስተባበር መከራዉንና ፈተናዉን መቋቋም ይኖርብናል ብለዋል ቅዱስነታቸው።

የዛሬ 30 ዓመት የነበረዉን ዓይነት አሰራር ዘርግቶ ቢሰራ ሰዉን ከረሀብ እልቂት ማዳን እንደሚቻልና ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ዙርያ በሰፊዉ ተወያይቶበት ዉሳኔ እንዲያሳልፍ በአጽናኦት በፓትሪያሪኩ በኩል ቀርቧል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤውን በዛሬው እለት የጀመረ ሲሆን ቤተክርስቲያኗ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 18 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ