የጉራፈርዳ ወረዳ ነዋሪዎች በጸጥታ ስጋት አካባቢያቸውን ጥለው እየተሰደዱ ነው ተባለ

0
90

በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ነዋሪዎች በጸጥታ ስጋት አካባቢያቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነ ተነገረ፡፡

በቤንች ሸኮ ዞን በተለይም በጉራፈርዳ ወረዳ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ  ታጣቂዎቹ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ በመሆኑ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰዎች አካባቢያቸውን ጥለው በመሸሽ ላይ እንደሆኑ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የመሸገው የሽፍታ ቡድን ቡድን ዜጎች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ታጣቂዎቹ ለህብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለጸጥታ አካሉም ጭምር የስጋት ምንጭ እንደሆኑ ቀጥለዋል ሲሉም ተናግረዋል አቶ ፍቅሬ አማን፡፡

እነዚህ ታጣቂ ቡድኖች ከአካባቢው ለማጥፋት የጸጥታ አካላት የተጠናከረ ስራ እየሰሩ ቢሆንም በአካባቢው ያለው የጸጥታ አካል በቂ  ባለመሆኑ ታጣቂዎቹ ለህብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለጸጥታ አካሉም ጭምር የስጋት ምንጭ እንደሆኑ አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ በዞኑ ያለው የጸጥታ ሁኔታ የሚያሰጋ ባይሆንም ህብረተሰቡ ግን ስጋት ላይ እንደወደቀ  የዞኑ አስተዳዳሪ ነግረውናል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 17 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ