የማሊ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ

0
74

የማሊ የሽግግር ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት ሰኞ ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አሁን ላይ በወታደራዊ መኮንኖች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ በርካታ ዓለም አቀፍ ቡድኖች በጋራ ባወጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡

የመሪዎቹ መታሰር ከአስር ዓመታት በላይ በሀገሪቱ የነገሰውን የፖለቲካ ውጥንቅጥ የሚያስቀጥል ነው፡፡

የማሊ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ባህ ንዳው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞክታር ኦዋን ከበርካታ ሰራተኞች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፣ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2020 ከተፈጸመው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በኋላ ማሊ ወደ ሲቪል አስተዳደር መመለሷን የሚከታተለው የሀገሪቱ የሽግግር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ ያመለክታል፡፡

ኮሚቴው የአፍሪካ ህብረትን ፣ በማሊ የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮን እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብን የሚያካትት ነው፡፡

ኮሚቴው ፣ ፈረንሳይ ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝ ፣ ጀርመን እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሽግግሩ ፕሬዝደንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በስራቸው የሚገኙ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡

ኮሚቴው እንዳለው በእስር ላይ የሚገኙት ባለሥልጣናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በፍጥነት እንዲለቀቁ እና እነርሱን በቁጥጥር ስር ያዋሉ ወታደራዊ አባላት ተጠያቂ እንዲሆኑም ተጠይቋል፡፡

ፕሬዝደንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታሰሩት ፕሬዝደንት ንዋድ ከፍተኛ የሚኒስትርነት ቦታዎች ላይ በተከታታይ እጩዎችን ይፋ ካደረጉ ብዙም ሳይቆይ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በማሊ ያለው ሁኔታ እንዲረጋጋ እና የማሊ ሲቪል መሪዎች እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል ተብለዋል፡፡

ጉተሬዝ በትዊተር ገፃቸው “በማሊ የሽግግር ወቅት የሲቪል አመራሮች መታሰራቸው ዜና በጣም አሳስቦኛል፡፡ መረጋጋት እንዲሰፍን እና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብለዋል፡፡

አሁን የተፈጸመው እስር ለሁለተኛ ጊዜ መፈንቅለ መንግስት እንዳይከሰት የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡

ፍራንስ 24 እንደዘገበው የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች እና የጦር መኮንኖች በመንግስት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል፡፡ የአሁኑ ሁኔታም እስከ መጪው ዓመት መጀመሪያ ድረስ ምርጫ ለማካሄድ በተገባው ቃል ላይ ጥርጣሬ ፈጥሯል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 17 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ