ከ500 በላይ ወጣቶች በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች ተያዙ – ሮይተርስ

0
174

የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች በትናንትናው ዕለት ምሽት በትግራይ ሰሜናዊ ክልል ሽረ ከተማ በአራት ካምፖች የነበሩ ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሚሆኑ ወጣት ሴቶችና ወንዶች በግዳጅ መያዛቸው ሶስት የእርዳታ ሰራተኞች እና አንድ ዶክተር ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡

ወታደሮቹ ሰኞ ዕለት 5 ስዓት ምሽት ገደማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በጭነት መኪና መወሰዳቸው ነው የተነገረው፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሐኪሙ በቦታው የነበሩ የአይን ምስክሮችን ቃል በመጥቀስ ብዙ ወጣቶች እንደተወሰዱ ነው የተናገሩት፡፡ ከእርዳታ ሰጪ ሠራተኞች መካከል አንዱ እንዳሉት ከሆነ በርካታ ወንዶች ተደብድበዋል ፣ ስልካቸው እና ገንዘባቸው ተወስዷል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ፣ በትግራይ ላይ የመንግስት ግብረ ኃይል ሀላፊ እና የትግራይ ክልላዊ ሀላፊ አስተያየት ለመጠየቅ በተደረገው ጥረት መልስ አልተሰጠንም ነው ያለው ሮይተርስ ፡፡

የሽረ ሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ አረጋይ ለሮይተርስ እንደገለጹት የጥቂቶቹ ዝርዝራቸው ቢኖሯቸውም በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች መወሰዳቸው ገልጽዋል፡፡

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በበኩላቸው “ተፈናቃዮችን ለመሰብሰብ” ምንም ምክንያት እንደሌለ የተናገሩ ሲሆን የይገባኛል ጥያቄዎቹ ከህዳር ወር ጀምሮ ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየተዋጋ ያለው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፕሮፓጋንዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ የአዉሮፓ ህብረት የሰብአዊ መብት አስተባባሪ ባወጣዉ መረጃ በትግራይ እየተካሄደ ባለዉ ጦርነት እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሞተዋል፤ 2 ሚልዮን ቤት ንብረታቸዉ ለቀዉ እንዲፈናቀሉ ተገደዋል፤ 91 በመቶ ወይም ወደ 6 ሚልዮን የሚጠጋዉ የክልሏ ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋል ብልዋል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 17 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ