አሜሪካ የጉዞ እገዳና ማዕቀቡን እንደገና ልታጤነው ትችላለች የሚል ተስፋ አለኝ- አምባሳደር ዲና

0
155

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስስተር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለስለጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ እገዳ ዝርዝር የለውም ፤ ዝርዝሩን በሂደት ነው የሚያወጡት እስካሁን አላወቅንም ሲሉ ተናገሩ።

አምባሳደሩ አሜሪካ የጣለችው እገዳና ማዕቀብ ከትግራይና ከኤርትራ ሰራዊት ጋር ከመያያዙ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከሌሎች የአሜሪካ ተፃራሪዎች ጋር ባላት ግንኙነት ምክንያት ሊሆን ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት አምባሳደሩ አዎ ሊሆን ይችላል ቻይና በሃገራችን ኢንዱስትሪ ስትሰራ ይደሰታሉ ማለት ከባድ ነው ብለው መልሰዋል።

የአሜሪካን ወሳኔ በተመለከተ ተጨማሪ ሀሳብ የሰጡቴ አምባሳደሩ ነገሩን ማጋጋልና ግንኙነቱ እንዲበላሽ አንፈልግም ፤ ነገር ግን አንድ ቀይ መስመሰር አለ፤ የኢትዮጵያ ነፃነት በገንዘብ፣ በአይኤምኤፍ ሆነ በምንም የሚለወጥ አይደለም ፤ መንግስት ቢፈቅድ የኢትዮጵያ ህዝብ አይፈቅድም ብለዋል።

የኢኮኖሚ ማዕቀቡ ምን ተፅዕኖ ያመጣብናል የሚለውን ነገሩን በሂደት እንየው ያሉት አምባሳደሩ ሲጀመር አሜሪካ በዚህ ሀገር ያላት ኢንቨስትመንት ምን ያህል ነው በየትኛው ዘርፍ ወዘተ የሚለው መጠናት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ውሳኔ ከህዳሴ ግድቡ ጋር ይገናኛል ወይ ተብለው የተጠየቁት አምባሳደር ዲና አዎ ይገናኛል ሲሉ መልሰዋል። አሜሪካኖች ስለህዳሴ ግድቡ ምን አገባቸው ሊባል ይችላል ነገር ግን ፍላጎት አላቸው ፤የምስራቅ አፍሪካው ተወካይ ጀፍሪ ፊልትማን የህዳሴ ግድቡን አጀንዳ በተለመከተ የኢትዮጵያ ያላትን አቋም ገዝተው እንደሄዱም ጠቁመዋል። በዚህም አሜሪካ ጉዳዩ በአፍሪካ ህብረት እንዲቀጥል አቋም ይዛለች።

አምባሳደር ዲና የማንጎበድድበት ደረጃ ላይ እንዳለን አሳውቀናል። ማንኛውም ኩሩ ሀገርና ነፃ ሀገር የሚያደርገው ኢኮኖሚ ስላለው ፣ሀብት ስላለው ሳይሆን ባለው ነፃነት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አምባሳደር ዲና የአሜሪካ ውሳኔ የሚተገበረው በምን ሂደት አልፎ ነው ለሴነት ውሳኔ ቀርቦ ነው ወይስ እንዲሁ ነው የሚለውን አልታወቀም ነገር ግን ውሳኒያቸውን እንደገና ያጤኑታል የሚል ተስፋ አለን ብለዋል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 17 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ