መንግስት በትግራይ ላይ መርዛማ ጋዝ ተጠቅመዋል የተበላውን ከእውነት የራቀ ነው – ኮ/ል ጌትነት አዳነ

0
218

ግንቦት 15/2013 ዓ.ም በእንግሊዝ እየታተመ በሚወጣ “ቴሌግራፍ” ጋዜጣ ላይ “ዊል ብራውን” እና “ሉሲ ካሳ” የተባሉ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ከወር በፊት ሚያዚያ 12/2013 ዓ.ም ተፈፀመ ብለው የዘገቡት የመርዛማ ጋዝ ጥቃት ሊሆን ቀርቶ ሊታሰብ የማይችል ነው ሲሉ የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ አስታወቁ።

ዘ ቴሌግራፍ ከትግራይ አገኝኃቸው ባላቸው ምስክሮች፤ ተጎጂዎች እንዲሁም በኬሚካሉ ምክንያት ሰዉነታቸው የተቃጠሉ ዜጎች በጋዜጣው አስፍረዋል። ይህም የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦር በሲቪል ማህበረሰቦች አከባቢ በከፍተኛ ሁኔታ የሚነድ መሳሪያ ተጠቅሞ ሊሆን ይችላል ሲል መግለጹ ይታወሳል።

መንግስት አሸባሪ ብሎ በሰየመው ህወሃት አሁንም በሃሰት ማደናገሩን ቢቀጥልም ፣ ከወር በፊት ግን በተለየ ውሸት ይፈበረክ እንደነበር ብዙ ማሳያዋች አሉ ሲሉ ነው ዳይሬክሩ የገለጹት።

“ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ህዝብን እየጨፈጨፈ ነው ፣ ሴቶች ተደፈሩ ፣ ሬሳ ገደል አስገቡ ፣ እርዳታ ተከለከለ ፣ ገበሬው እርሻ እንዳያርስ ተደረገ ፣ ንብረቱ ወደመና ተዘረፈ አልፎም የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ታገቱና ተገደሉ ” እያሉ ራሳቸው የፈፅሙትን ድርጊት አስመስለው በመቅረፅ ጭምር ሲያሰራጩ ቆይተዋል ሲሉ ነው ኮ/ል ጌትነት የገለጹት፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በግንቦት 13/2013 ዓ.ም ባወጣው የምርመራ ውጤት በአከሱም በተደረጉ ግድያዎች ላይ መሰረት አድርጎ የወታደራዊ ግዴታ በሌለበት ወቅት በግድያ የተጠረጠሩ 28 የኢትዮጵያ ወታሮች ላይ ክስ መመስረቱን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም ጾታዊ ጥቃትና አስገድዶ መድፈር የፈጸሙ 25 ወታደሮችም ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል አቃቤ ህግ፡፡ በክሶቹ ላይ በአጭር ጊዜ ፍርድ እንደሚሰጥ አቃቤ ህግ ገልጾ ነበር፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ዛሬ ባወጣው መግለጫው ይህን አይነት የበሬ ወለደ ውሸት የሚያስተናግዱ ሚዲያዎችና ግለሰቦች አንድም ለቆየ ዓላማቸው ፤ በሌላም ኢትዮጵያ በተዘረፈችው ዶላር የተገዙ ነጭ ሸብር ፈጣሪዎች ናቸው ሲሉ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሃገራችን የጅምላ ጨራሽ ጦር መሳሪያዎችን ያለመጠቀምና ያለማስተላለፍ አለም አቀፍ ስምምነትን የፈረመች እና ያፀደቀች ቀዳሚ ሃገር ነች ። በወራሪዎችም የጥቃቱ ሰለባ እንደነበርን የወጋ ቢረሳ… የተወጋ እንዲህ ሲነካካ ያስታውሳል ነው ያሉት ።

የአሁኑ መርዛማ ጋዝ ፣ የውጭው ወሬና ጫና መሆኑ ታውቆ ፤ በአንዳንድ ቅጥረኛ ሚዲያ የሚሰራጭ ዘመቻን በተገቢው ልክ ስለምንረዳ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እንደ ቀደሙት አያት ቅደመ አያቶቻችን ጠብቀን እኛም ለመጭው ትውልድ ጀግንነትን እናወርሳለን ብለዋል ኮ/ል ጌትነት አዳነ።

ቴሌ ግራፍ በዘገባው እንዳስነበበው ከሆነ ከተጎጂዎቹ መካከል በማዕከላዊ ትግራይ የ ‘ዓዲ አይቆሮ’ መንደር ነዋሪ የሆነች የ13 ዓመት ታዳጊ ቅሳነት ገብረሚካኤል የምትገኝበት ሲሆን ሚያዚያ 20 መኖሪያ ቤታቸው ጥቃት ሲሰነዘርበት ከፍተኛ ቃጠሎ ደርሶባታል ብሏል።

ታዳጊዋን በስልክ እንዳነጋገሯትና ቃጠሎው ከደረሰባት በኋላ ወደ ሆስፒታል ሄዳ የተነሳችው ፎቶ የእጇ፣ የእግሯ እና የፊቷ ቆዳ መቃጠሉን እንደሚያሳይ ዘገባው ይገልጻል።

ነገርግን መከላክያ ሰራዊት ይህ ሁሉ ዘ ቴሌግራፍ ይዞት የወጣው ዘገባ ውሸት ነው አለ፡፡

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ