የናይጄሪያ የጦር ኃላፊ ጄኔራል ኢብራሂም በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው አለፈ

0
21

የናይጄሪያ የጦር ኃላፊ ጄኔራል ኢብራሂም አታሂሩ በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

ኃላፊው በሰሜን ምዕራብ በምትገኘው ካዱንጋ ግዛት አውሮፕላኑ ተከስክሶ መሞታቸውን ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።

አውሮፕላኑ አስቸጋሪ በተባለ አየር ሁኔታ ለማረፍ ሲሞክር መከስከሱን ጦሩ ገልጿል።

በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት አስር ወታደሮችና እንዲሁም የአውሮፕላኑ ሰራተኞችም ሞተዋል።

የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ በኃላፊው ሞት የተሰማቸውን ኃዘን የገለፁ ሲሆን “በአደጋው ጥልቅ ኃዘን ተሰምቶኛል” በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የ54 አመቱ ጄኔራል ኢብራሂም አታሂሩ ይህንን ሹመት ያገኙት በያዝነው አመት ጥር ወር ላይ እንደሆነና ከፍተኛ ሹመትም ነው ተብሏል።

መንግሥት ከአስር አመታት በላይ የሚታገለውና ተገንጣይ የሚላቸውን የጂሃዲስት ታጣቂዎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማንበርከክ ጦሩ መጠንከር አለበት የሚለው እቅድ ነው። ከዚህም እቅድ ጋር ተያይዞ ናይጄሪያ ጦሯን እያጠናከረች ነው ተብሏል።

የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት አደጋው “አገራችን የተደቀነባትን የደህንነት ችግሮች ለመቅረፍ ከምታደርገው ግብግብ መሃል ላይ መሆኑ ከፍተኛ ውድመት ነው” ብለዋል።

የናይጄሪያ አየር ኃይል እንዳሳወቀው አደጋው የተከሰተው አውሮፕላኑ ካዱና አለም አቀፍ አየር መንገድ እያረፈ በነበረበት ወቅት ነው።

ይህ አርብ እለት የተከሰከሰው የጦር አውሮፕላን ለናይጄሪያ የመጀመሪያዋ አይደለም።

ከሶስት ወራትም በፊት የናይጄሪያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። በወቅቱ አውሮፕላኑ ከመዲናዋ አቡጃ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ተከስክሷል ተብሏል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 14 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ