ያለፉት ሶስት አመታት በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ተስፋም ስጋትም የተፈራረቁባቸው ነበሩ ተባለ

0
34

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጠን ከመጡ ወዲህ በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የታዩ ለውጥና ጉድለቶች በጥናት ተደግፈው ቀርበው ምክክርም እየተደረገባቸው ነው፡፡

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ህብረት ያስጠናቸው ሰብአዊ መብትን የተመለከቱ ሰባት የጥናት ፅሁፎች እስከ ነገ በሚቆየው መድረክ ቀርበው ምክክር ሊደረግባቸው ፕሮግራም ተይዞላቸዋል፡፡

እስካሁን ከቀረቡ የጥናት ውጤቶች የሚበዙት እንደሚያሳዩት ከ2010 እስከ 2011 መጨረሻ ያለው የጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ የስልጣን ዘመን የመጀመሪያ አንድ አመት በተለያየ መለኪያ ስኬታማ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡

ከዚያ በኋላ ያለው የሁለት አመት ጊዜ ግን የተለያየ ምክንያት ቀስ በቀስ ክልከላና እቀባ የታየበት ነበር ብለዋል የቀረቡት ጥናቶች፡፡

ሰባቱ የጥናት ፅሁፎች የመሰብሰብና የመደራጀት ነፃነት ፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና መረጃ የማግኘት ነፃነት ፣ ከቦታ ቦታ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት ፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሁኔታ ፣ የሴቶች መብት ፣ የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ እንዲሁም በግጭቱ ወቅት የተጠያቂነት መንገዶች በሚሉ ሀሳቦች ዙሪያ የተሰሩ ናቸው፡፡

ሁሉም የጥናት ፅሁፎች ከ2010 አጋማሽ በኋላ ያለውን የሶስት አመት ጊዜ በተለያየ መንገድ በመለካት የተሰሩ መሆናቸውን በዝግጅቱ ላይ ተነግረዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አመታት ላይ ሁሉም የራሱን መለኪያ መንገድ ያቀርባል ጊዜውን አንዳንዱ የስኬት ፣ አንዳንዱ ደግሞ የችግር አድርጎ ሲያቀርብ ይታያል፡፡

ሁሉንም ነገር በጥናት አስደግፎ ማቅረብ ሲቻል ግን እውነታውን በቅጡና በበጎ ለመረዳት ያስቻላል ብለዋል ጥናቱን ያስጠናው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር አቶ መስኡድ ገበየሁ ፡፡

የሰብአዊ መብትን የተመለከቱ የህግ ማዕቀፎች ዘሪያ ባለፉት ሶስት አመታት በርከት ያሉ ለውጦች መደረጋቸው የተነሳ ሲሆን ገና መሻሻልና መፍታታት በርከት ያሉ ለውጦች የሚገባቸው በዛ ያሉ ስራዎችን ይቀራሉም ተብሏል፡፡

እንደ ምሳሌ በመሰብሰብና የመደራጀት ነፃነት ዙሪያ በቀረበው ጥናት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና መሰብሰብ ፣ ሰብአዊ መብት ቢሆንም ባለፉት ሶስት አመታት በዛ ያሉ የታቀዱ ሰልፎች በደፈናው ሲከለከሉ ቆይተዋል ተብሏል፡፡

ይህም የሆነው አንድም ቀደምው የተደረጉ ሰልፎች የግጭትና ሞት መነሻ በመሆናቸው ምክንያት ስጋት በመፈጠሩ አንድም በመንግስት ላይ የሚደረገው ተቃውሞ በመበርታቱና ስጋትም በመፈጠሩ ነው ያሉት ጥናት አቅራቢዎቹ በህጉ ሰልፍ ለማድረግ ለከተማ መስተዳደር ወይምን ለወረዳ መስተዳደር ማሳወቅ የሚል አሰራር ቢኖርም በተለያዩ አጋጣሚዎች ማሳወቅ የሚለው ሀሳብ መፍቀድ በሚል ተተክቶ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ሰልፎች አለበቂ ምክንያት አልተፈቀዱም ተብሎ ሲከለከል ቆይቷል ተብሏል፡፡

እነዚህና ሌሎችም ጉዳዮች በቂ የህግ ማፍታቻና ማሻሸያ የሚፈልጉ ናቸው ተብሎ በምሳሌነት ተነስተዋል፡፡

በተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የተሰሩት እነዚህ ሰባት ጥናቶች እስከ ነገ በሚቆየው መድረክ ቀርበው ምክክር ከተደረገባቸው በኋላ የታዩ ችግሮች ተነቅሰው ማሻሻያና ለውጥ እንዲደረግባቸው ግፊት የማድረግ ስራ ይጀመራል ሲል ሸገር ሬድዮ ዘግቧል፡፡

አውሎ ሚድያ ግንቦት 13 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ