አዲስ ገቢ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲዎች እንዲገቡ ይደረጋል- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

0
64

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት አሟልተው የተገኙ ተማሪዎች በተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች እስከ ግንቦት 30 ድረስ እንዲገቡ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ አስታወቁ።

የዘንድሮውን የመመዘኛ ፈተና ካለፉት ከ147 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 206 ተማሪዎች በሚፈልጉት  የትምህርት መስክ እና የትምህርት ተቋም እንዲመደቡ መደረጉንም ሚኒስትሩ  ገልጸዋል።

ከምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታ ካቀረቡ 23 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከልም ከ1 ሺ 8 መቶ በላይ የሚሆኑት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ የምደባ ማስተካከያ መደረጉንም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አንስተዋል።

የትምህርት መስክ ምርጫን አስመልክቶ በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረም 386 ተማሪዎች በመረጡት ዘርፍ እንዲመደቡ ተደርጓል።

ከፍተኛ የጤና እክል ያለባቸው፣ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች፣ነፍሰጡር እና ከሁለት አመት በታች ልጅ ያላቸው እናቶች፣አካልጉዳተኞች እና ከአርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ቅሬታን በማየት በቂ ማስረጃ ላቀረቡት አዎንታዊ ምላሽ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል የትምህርት ተቋም ምርጫን በሚመለከት ርቀትን፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መሰረት አድርገው የቀረቡ ጥያቄዎችን ውድቅ ማድረጉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል ሲል ፋና ቲቪ ዘግቧል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 13 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ