ለኤምባሲዎቹ ሊደርስ የነበረው የተቃውሞ ደብዳቤ ኤምባሲዎች ዝግ በመሆናቸው ቀረ ተባለ

0
23

በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ደብዳቤ ለኤምባሲዎቹ ለማስገባትና በግንባር ለመነጋገር ተይዞ የነበረው መርሐ ግብር መስተጓጎሉንም የተቃውሞው አደራጆች አስታውቀዋል::

ኢትዮጵያውያን የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በያሉበት ሆነው ድምጻቸውን የሚያሰሙበት መርሃ-ግብር ዛሬ ይካሄዳል፡፡

የተቃውሞ ድምጽ የማሰማት መርሐ ግብሩ “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ” በሚል መሪ ሐሳብ በያሉበት ሆነው ለአንድ ሰዓት መልዕክታቸውን የሚያስተላልፉበት ነው።

መርሃ-ግብሩ “ብሔራዊ ክብር በሕብር” የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ንቅናቄውን ያዘጋጁት ከማህበረሰብ አንቂዎች፣ አርቲስቶች፣ ሲቪክ ማህበራትና ታዋቂ ግለሰቦች የተወጣጡ ናቸው።

የመርሃ ግብሩ አስተባባሪ አብይ ታደለ በሰጡት መግለጫ፤ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ማንኛውም ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ ባለበት እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ በማለት ድምጹን እንዲያሰማ አስታውቋል።

በአንድ ሰዓቱ መርሃ-ግብር “ብሔራዊ ክብር በሕብር”፣ “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ”፣ “የውጭ አገራት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማክበር አለባቸው”፣ “የውጭ አገራት ጣልቃ ገብነታቸውን ያቁሙ”፣ “የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ከማከናወን የሚያግደን ሃይል የለም” እና “ምርጫውን ማካሄድ የውስጥ ጉዳያችን ነው” የሚሉ ሐሳቦችን ያዘሉ መልዕክቶች ይተላለፋሉ ተብሏል።

በዚህም ዜጎች የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም እንዲሁም በአደባባይ በመውጣት መልዕክታቸውን ማስተላለፍ እንደሚችሉ ነው አቶ አቢይ የገለጹት።

ከታዋቂ ግለሰቦችና አርቲስቶች የተወጣጡ ግለሰቦች በአዲስ አበባ በሚገኙ ኤምባሲዎች በመሄድ የተዘጋጁ ደብዳቤዎችን እንደሚያስገቡ መርሃ ግብር የተያዘ ቢሆንም ኤምባሲዎች ዝግ ስለሆኑ መሄድ እንዳልተቻለም ነው ያስታወቁት።

ጉዳዩ የፖለቲካ ፣ወይም የመንግስት አይደለም ያሉት አስተባባሪው፤ ወደ ኤምባሲዎች በቀጠሮ ሄደን መልዕክታችንን ልናስረዳ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ጸባችን ከሌሎች ሀገራት ህዝቦች ጋር ሳይሆን ከሀገራቱ ከመንግስታት ጋር ነው ያሉ ሲሆን፤ ኤምባሲዎች አካባቢ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ እና ንቅናቄው የታለመለትን ግብ እንዲመታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል ሲል አል ዐይን ዘግቧል።

አውሎ ሚድያ ግንቦት 13 / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ